ኢንስቲትዩቲ የተግባር ተኮር ስልጠና ጥራትን ለማስጠበቅ ከባለድርሻ አካላት ጋር እየመከረ ነው።

ቱሪዝም ማሰልጠኛ ኢንስቲትዩት በተቋሙ ውስጥ እየሰጠ ከሚገኘው ስልጠና ባለፈ በትብብር ስልጠና ዘዴ በዘርፉ ከተሰማሩ ሆቴሎች እና ማህበራት ጋር ምክክር እያደረገ ነው።
የምክክር መድረኩን የከፈቱት የኢንስቲትቱ ዋና ዳይሬክተር አቶ ጌታቸው ነጋሽእንደገለጹት ኢንስቲትዩቱ ባደረገው በዘርፉ የሰለጠነ የሰው ሀይል ጥናት ውጤት በዘርፉ ውስጥ 47 በመቶ ያህሉ በሆቴልና በአስጎብኚ ድርጅቶች ላይ ተሰማርቶ እንደሚገኝ ጠቅሰዋል።
በቱሪዝም ዘርፉ አሁንም ያለው የሰለጠነ የሰው ሃይል ከ50በመቶ በላይ ማድረስ አለመቻሉ በኢንደስትሪው የአገልግሎት አሰጣጥ ላይ ክፍተት ያሳያል ብለዋል።
በዚህ የምክክር መድረክ በአጫጭር ስልጠና የተዘጋጁ ሞጁሎችን ማስተዋወቅና የባለድርሻ አካላት ውይይት እንዲያደርጉበት የተዘጋጀ በመሆኑ የነቃ ተሳትፎ እንዲያደርጉ ጥሪ አስተላልፈዋል።
ዋና ዳይሬክተሩ አክለውም የዛሬው የምክክር መድረክ ቅንጅታዊ አሰራር የሚጠናከርበት በዘርፉ ያሉ ችግሮቾን በመለየት ውጤታማ የምንሆንበት ነው ብለዋል፡፡
የትብብር ስልጠና አሰራር ላይ ሰነድ ያቀረቡት የትብብር ስልጠና አስተባባሪ አቶ ታደሰ ሞላ ኢንስቲትዩቱ ወደ ሆቴሎችና አስጎብኝ ድርጅት የሚልካቸው ሰልጣኞች ትክክለኛ የተግባር ስልጠና እንዲያገኙ ማድረግና ትክክለኛ ምዘና በማድረግ በተዘጋጀው ፎርማት መሰረት ሞልቶ ለተቋሙ መላክ የትብብር ስልጠና ውጤታማ ያደርጋል ብለዋል፡፡
ትክክለኛ መረጃዎችን ለማግኘት የሚከተሉትን ማስፈንጠሪያዎችን ይጠቀሙ
ፌስቡክ፡ https://www.facebook.com/tticommunication
ቴሌግራም ፡https://t.me/tticommunication
ዌብሳይት፡ https://www.tti.edu.et/