የውጭ ሀገር ሥራ ስምሪት ስልጠና ለሚሰጡ አሰልጣኞች የአቅም ግንባታ ስልጠና እየተሰጠ ነው ።

የፌዴራል ቱሪዝም ማሰልጠኛ ኢንስቲትዩት ከተለያዩ ክልሎች ለተወጣጡ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጆች በውጭ ሀገር ሥራ ስምሪት ሥልጠና ለሚሰጡ አሰልጣኞች የአቅም ግንባታ ስልጠና እየተሰጠ ነው።
በሥልጠናው የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የተቋሙ ዋና ዳይሬክተር አቶ ጌታቸው ነጋሽ እንደገለጹት ይህ አቅም ግንባታ ስልጠና መንግስት ለውጭ ሀገር ስራ ስምሪት የሰጠውን ትኩረት ለማሳካት እና ዜጎች ያለስልጠና ወደ ውጪ በመሄድ የሚደርስባቸውን ያልተመጣጠነ ክፍያ ለማስተካከል እንደሆነና በሀገር ደረጃም ተመሳሳይ ደረጃ ኖሮ ስልጠና የሚሰጡ አካላትን ግንዛቤ ከፍ ለማድረግ ታስቦ እንደሆነ ገልጸዋል።
የተቋሙ ስልጠና እና አቅም ግንባታ ዘርፍ ም/ዋና ዳይሬክተር አቶ ሀብታሙ ክብረት በበኩላቸው ከዚህ በፊት በሁለት ዙር በተለያዩ ክልሎች ያሉ የውጭ ሀገር ሥራ ስምሪት ለሚያሰለጥኑት አሰልጣኞች በተሰጠው ስልጠና የመጣው ግብረመልስ ጥሩ እንደሆነና ዜጎች በአቅራቢያቸው ስልጠና በማግኘት ከሥራ አጥነት በመላቀቅ መንግስት ባመቻቸው እድል እየተጠቀሙ ነው ብለዋል።
ዘንድሮ የውጭ ሀገር ሥራ ስምሪት ለሚሰጡ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጆች የአሰልጣኞች ስልጠና ለመስጠት ከታቀደው 85 በመቶ መከናውኑም ተጠቅሷል።
የተቋማችን አሰልጣኝ አቶ አዶናይ አጥናፉ በምግብና መጠጥ መስተንግዶ የንድፈ ሃሳብና የተግባር ስልጠና ተሰጥቷል ።
ስልጠናው በተለያዩ ርዕሶች ለሦስት ቀን በተለያዩ የኢንስቲትዩቱ አሰልጣኞች የሚቀጥል ይሆናል።
ትክክለኛ መረጃዎችን ለማግኘት የሚከተሉትን ማስፈንጠሪያዎችን ይጠቀሙ
ፌስቡክ፡