በሆቴልና ቱሪዝም ሥልጠና ዘርፍ በስምንት የሙያ ደረጃዎች ማሻሻያ እየተደረገ ነው
በቱሪዝም ማሰልጠኛ ኢንስቲትዩት እና በሥራና ክህሎት ሚኒስቴር የቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ስልጠና ኤጀንሲ የጋራ ትብብር በሆቴልና ቱሪዝም ሥልጠና ዘርፍ በስምንት የሙያ ደረጃዎች ማሻሻያ እየተደረገ ነው።

በሥራና ክህሎት ሚኒስቴር የቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ስልጠና ኤጀንሲ ኢንዱስትሪ ሞቢላይዜሽን ፣ ሙያ ደረጃና ብቃት ምዘና ዳይሬክተር ወ/ሮ ንግስት መላኩ እንደገለፁት የሆቴልና ቱሪዝም ዘርፍ ሙያ ማሻሻያ ከዛሬ አስር ዓመት በፊት በተሰራበት እስከ አሁን እየተሰራ በመሆኑ ብዙ ችግሮች ያሉበት በመሆኑ ይህን ችግር የሚፈታ ማሻሻያ ይሰራል ተብሎ እንደሚጠበቅ ተናግረዋል፡፡
በዚህ የሙያ ማሻሻያ መርሃ ግብር የዘርፉ ባለድርሻ አካላት የተሳተፉ ሲሆን ማሻሻያ የሚደረግባቸው የሙያ ዘርፎች የሚከተሉት ናቸው
* food & Beverage serves የምግብ እና መጠጥ መስተንግዶ
* food & Beverage control የምግብና መጠጥ ቁጥጥር
* Housekeeping laundry service የቤት አያያዝና ላውንደሪ
* Front office service እንግዳ አቀባበል
* Tour Guide ቱር ጋይድ
* Tour Operation ቱር ኦፕሬሽን
* Baker and pastry production የዳቦና ኬክ ዝግጅት
* Culinary art የምግብ ዝግጅት
በነዚህ ሙያዎች የዘርፉ የሥራ ደረጃ በኢንዱስትሪው ባለሙያዎች ፣ ባለድርሻ አካላት እና የማሰልጠኛ ኢንስቲትዩቱና ከፌዴራል ትምህርትና ስልጠና ኤጀንሲ ባለሙያዎች ተሳታፊ እንደሆኑ የማሰልጠኛ ኢንስቲትዩቱ አካዳሚክ ዲን አቶ አብርሃም ለገሰ ገልጸዋል።