ኢንስቲትዩቱ ወቅቱ የሚፈልገውን ስልጠና ለመስጠት አዳዲስ የማሰልጠኛ ሰነዶች ማዘጋጀቱ ተገለጸ።

ቱሪዝም ማሰልጠኛ ኢንስቲትዩት ለሀገራችን ሆስፒታሊቲ እንዱስትሪ ወቅቱ የሚጠይቀውን ስልጠናዎች ለመስጠት የሚያስችል አዳዲስ የማሰልጠኛ ሰነዶች ተዘጋጅተዋል። የኢንስቲትዩቱ ሥልጠናና አቅም ግምባታ ዘርፍ ም/ዋና ዳይሬክተር አቶ ሀብታሙ ክብረት ገልጸዋል፡፡
በሀገራችን ሆስፒታሊቲ እንዱስትሪ ውስጥ በአጭርና በረጅም ጊዜ ሥልጠና ብቃት ያለውን የሥራ መሪና ባለሙያ በመፍጠር የተሻለ አገልግሎት ለመስጠት እንዲያስችል ያለውን ወቅታዊ ሁኔታ ታሳቢ በማድረግ የተዘጋጁ መሆኑን የገለጹት ም/ዋና ዳይሬክተሩ በዘርፉ የተሰማሩ ድርጅቶች ለሙያው ተገቢውን ትኩረት መስጠት ይገባል ብለዋል፡፡
የስልጠና ማኑዋሎቹ ጥናት ላይ የተመሰረተ መሆኑን የገለጹት የጥናት ምርምርና ማማከር ዘርፍ ም/ዋና ዳይሬክተር አቶ ይታሰብ ሥዩም ይህን መሰረት በማድረግ ደረጃውን የጠበቀ የማማከር አገልግሎት መስጠት መጀመሩን ገልጸዋል፡፡ ኢንስቲትዩቱ በራሱ ተነሳሽነት የማማከር አገልግሎት እየሰጠ እንደነበር የተናገሩት አቶ ይታሰብ ሥዩም ሆቴሎችና በዘርፉ የተሰማሩ ድርጅቶች በተመጣጣኝ ክፍያ አገልግሎት ይሰጣል ብለዋል፡፡
ኢንስቲትዩቱ አዳዲስ በተዘጋጁት የስልጠና ማኑዋሎችን በሚመለከት እና ከባለድረሻ አካላት ጋር ስለሚሰሩ ጉዳዮች ምክክር ማድረጉ ይታወሳል፡፡
የተዘጋጁ የስልጠና ማኑዋሎች
1. Leadership For Hotel Managers
2. Culinary Art Leadership Management
3. Food and Beverage Management
4. Quality Customer Service Management
5. Digital Literacy for Hospitality
6. Ethiopian Traditional Food Preparation
7. Wellness and Spa Service
8. Hotel Software
ትክክለኛ መረጃዎችን ለማግኘት የሚከተሉትን ማስፈንጠሪያዎችን ይጠቀሙ
ፌስቡክ፡ https://www.facebook.com/tticommunication
ቴሌግራም ፡https://t.me/tticommunication
ዌብሳይት፡ https://www.tti.edu.et/