የኢንዱስትሪ አሰልጣኞች የማሰልጠን ስነ ዘዴ ስልጠና ተጠናቀቀ።
ለሁለት ቀን ሲሰጥ የቆየው የኢንዱስትሪ አሰልጣኞች የማሰልጠን ስነ ዘዴ ስልጠና ተጠናቀቀ።
በማጠቃለያው ፕሮግራም ላይ የተገኙት የኢንስቲትዩት ትብብር ስልጠና አስተባባሪ ና አሰልጣኝ ታደሰ ሞላ እንደገለፁት ይህ ስልጠና በዚሁ የሚቀር ሳይሆን በቀጣይነት ወደ ተግባር የሚቀየር እንደሆነ በመጠቆም አሰልጣኞቻችን ወደ ኢንዱስትሪ በሚሄዱበት ወቅት የሚገጥማቸውን ክፍተቶች ለመሙላት አሁን ከሰለጠኑ ባለሙያዎች የሚጠበቅ መሆኑን ገልጸዋል።
የዛሬውን ስልጠና የሰጡት የተቋማችን አሰልጣኝ ወ/ሪት እታፈራሁ ሲሳይ የመምህሩ የማስተማሪያ ሰነድ አዘገጃጀትና በውስጡ መካተት ያለባቸው ተግባራት እንዲሁም ሰልጣኙን እንዴት መገምገም እንደሚቻል በተግባር የተደገፈ ስልጠና ሰጥተዋል።
ለሰልጣኞቹ በስልጠናው ዙሪያ መመዘኛ በመስጠት ሰርተፍኬት ተሰጥቷቸዋል።
ሰልጣኞችም በስልጠናው በጣም እንደተደሰቱና ከተቋሙ ጋር በትብብር ስልጠናም ይሁን በሌላ አብሮ እንደሚሰሩ ገልጸዋል።
https://t.me/tticommunication
Recent Comments