ወጣቶች የራሳቸውን የስራ ዕድል እንዲፈጥሩ በቱሪዝም ዘርፍ ያለውን የስራ ዕድልን በሚመለከት የግንዛቤ ማስጨበጫና የተግባር ስልጠና እየተሰጠ ነው።
ማሰልጠኛ ኢንስቲትዩቱ ከቂርቆስ ክ/ከተማ ወረዳ 10 እና 11 ለተወጣጡ ስራ ፈላጊ ሴቶችና ወጣቶች በቱሪዝም ዘርፍ ያለውን የስራ ዕድል የግንዛቤ ማስጨበጫና የተግባር ስልጠና እየሰጠ ይገኛል።
ቱሪዝም ማሰልጠኛ ኢንስቲትዩት በማህበረሰብ አቀፍ አገልግሎት በአካባቢው ላይ የሚገኙትን ማህበረሰብ ተጠቃሚ የሚያደርጉ ስራዎችን እየሰራ እንደሚገኝ የተናገሩት የኢንስቲትዩቱ ጥናት ምርምርና ማማከር ዘርፍ ም/ዋና ዳይሬክተር አቶ ይታሰብ ሥዩም የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠናቸውን ካጠናቀቁ መስራት በሚፈልጉት የሙያ መስክ ተጨማሪ የአጫጭር ጊዜ ስልጠናዎች ይሰጣቸዋል ብለዋል።
ኢንስቲትዩቱ ባለፈው ዓመትም ክ/ከተማው ላደራጃቸው መንገድ ዳር ምግብ አዘጋጅቶ መሸጥ ላይ መሰማራት ለፈለጉ ወጣቶች ድጋፍ ማድረጉን ያስታወሱት ም/ዋና ዳይሬክተሩ በወሰዱት የግንዛቤ ትምህርት ሊሰማሩበት የሚፈልጉትን ሙያ ለይቶ የአጫጭር ጊዜ ስልጠናና የግብዓት ድጋፍ ያደርግላቸዋል ብለዋል።
በምግብ ዝግጅት ሙያ ለመሰማራት ለፈለጉ ወጣቶች የተግባር ስልጠና እየተሰጠ የሚገኝ ሲሆን በአሁኑ ዙር 60 ለሚሆኑ የተግባርና የግንዛቤ ማስጨበጫ እየተሰጠ ይገኛል ።
ትክክለኛ መረጃዎችን ለማግኘት የሚከተሉትን ማስፈንጠሪያዎችን ይጠቀሙ
ፌስቡክ፡ https://www.facebook.com/tticommunication
ቴሌግራም ፡https://t.me/tticommunication
ዌብሳይት፡ https://www.tti.edu.et/
Recent Comments