ኢንስቲትዩቱ እየሰጠ በሚገኘው አገልግሎት ላይ የተገልጋይ እርካታን ለመጨመርጰ የችግር አፈታትና ውሳኔ አሰጣጥ ላይ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና መሰጠት ጀመረ።

የቱሪዝም ማሰልጠኛ ኢንስቲትዩት እየሰጠ በሚገኘው የስልጠና፣ የምርምርና ማማከር አገልግሎቶች ላይ የደምበኞችን እርካታ ከፍ ለማድረግ እንዲያስችል ለሰራተኞችና ማኔጅመንት አባላት በችግር አፈታትና ውሳኔ አሰጣጥ ላይ በ #EASTRIP ፕሮጀክት አስተባባሪነት የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና እየተሰጠ ይገኛል።
ስልጠናውን ያስጀመሩት የኢንስቲትዩቱ የአመራርና አስተዳደር ዘርፍ ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ ገዛኸኝ አባተ ስልጠናው ሁሉም ሰራተኛ በተመደበበት ቦታ የበላይ አመራር ሳይጠብቅ ሀላፊነት እንዲወጣ እና ባለሙያው የሚያጥሙ ችግሮችን ለመፍታት የሚያግዝ እንደሆነ በመጠቆም ስልጠናው በቂ የልምድ ልውውጦች የሚደረጉበት ነው ብለዋል።
ትክክለኛ መረጃዎችን ለማግኘት የሚከተሉትን ማስፈንጠሪያዎችን ይጠቀሙ
ፌስቡክ፡ https://www.facebook.com/tticommunication
ቴሌግራም ፡https://t.me/tticommunication
ዌብሳይት፡ https://www.tti.edu.et/