ፕሮጀክቱ ከሰራተኞች አቅም ማጎልበቻ ባሻገር ኢንስቲትዩቱ የልህቀት ማዕከል ለመሆን እየሰራ የሚገኘውን እቅድ ለማሳካት ከፍተኛ ድጋፍ እያደረገ እንደሚገኝ ተገለጸ፡፡

EASTRIP ፕሮጀክት ከሰራተኞች አቅም ግንባታ ባሻገር ለኢንስቲትዩቱ የተሰጡ ተልዕኮዎችን እንዲሁም ከትላንት ጀምሮ በተሰጠው ስልጠና ወቅት የተለዩ ችግሮችን በመፍታት ተልዕኮውን እንዲወጣ አስፈላጊውን ሁሉ ድጋፍ እያደረገ እንደሚገኝ የፕሮጀክቱ አስተባባሪ አቶ አብርሀም ለገሰ ገለጹ።
ከታህሳስ 26 ጀምሮ እየተሰጠ ነበረው የችግር አፈታትና ውሳኔ አሰጣጥ ስልጠና መጠናቀቁን ተከትሎ ስልጠናው በተቋም ደረጃ የሚታዩ ወቅታዊ ጉዳዮችን ለመተንተና ችግሮችን ለመለየት የሚያግዝ እንደሆነ የገለጹት አቶ አብርሃም ለገሰ ተመሳሳይ አቅም ግንባታ ስልጠናዎች በቀጣይነት ይሰጣሉ ብለዋል።
ከዚህም ባለፈ ፕሮጀክቱ የኢንዱስትሪውን ፍላጎት መሰረት ያደረጉ፣ የኢንዱስትሪውን ችግር ለመፍታት የሚያስችሉ ጥናት ላይ የተመሰረቱ የስልጠና ማኑዋሎች እንዲዘጋጁ ማድረጉን ያስታወሱት የፕሮጀክቱ አስተባባሪ ኢንስቲትዩቱ ከባለድርሻ አካላት ጋር ተቀራርቦ እንዲሰራ፣ ስልጠናዎች በቴክኖሎጂ የተደገፉ እንዲሆኑ በአጠቃላይ ኢንስቲትዩቱን ወደ ልህቀት ማዕከል ሊያሻግሩ የሚያስችል ድጋፍ እየተደረገ እንደሆነ አብራርተዋል ።
ስልጠናው ላይ ከተሳተፉት መካከል የቮኬሽናል ጋይዳንስና ትብብር ስልጠና አስተባባሪ አቶ ታደሰ ሞላ በበኩላቸው የተሰጠው ስልጠና ቱሪዝም ማሰልጠኛ ኢንስቲትዩት ምቹ የስራ ቦታን ለመፍጠር እየሰራና የሪፎርም ስራዎች እየተካሄዱ ባለበት በመሆኑ ወቅታዊ እንደሆነ ገልጸዋል።
በማሰልጠኛ ኢንስቲትዩቱ ውስጥ የታቀዱ ስራዎች ሁሉንም በሚያሳትፍ መልኩ መረጃዎችን ተደራሽ ማድረግ ጉዳዩ የሚመለከታቸውን ሰራተኞች በቀላሉ ለማሳተፍ ያግዛል ያሉት አቶ ታደሰ ሞላ የተቋሙ እቅዶችን ለማሳካት በቅንጅት መስራት አስፈላጊ ነው ብለዋል።
በስልጠናው ላይ በግብዓት፣ በቅንጅታዊ አሰራር፣ እቅድን መሰረት አድርጎ ከመስራትና ሌሎችም ኢንስቲትዩቱ ተልዕኮውን በአግባቡ እኔዳይወጣ በሚያደርጉ ጉዳዮች ላይ ሰፊ ውይይት የተደረገ ሲሆን ሰራተኞችም በቀጣይነት የተሻለ አገልግሎት ለመስጠት ያላቸውን ቁርጠኝነት ገልጸዋል።
ትክክለኛ መረጃዎችን ለማግኘት የሚከተሉትን ማስፈንጠሪያዎችን ይጠቀሙ
ፌስቡክ፡ https://www.facebook.com/tticommunication
ቴሌግራም ፡https://t.me/tticommunication
ዌብሳይት፡ https://www.tti.edu.et/