ኢትዮጵያ የዓለም አቀፉ የክህሎት ድርጅት ሙሉ አባል ሆነች።
ኢትዮጵያ የዓለም አቀፍ የክህሎት ድርጅት አባል መሆኗ በርካታ ኢኮኖሚያዊ፣ ፓለቲካዊ እና ማህበራዊ ፋይዳ እንዳለው የገለጹት የሥራና ክህሎት ሚኒስትር ወ/ሮ ሙፈሪያት ካሚል
ሀገራችን በክህሎት ልማት ከተቀረው ዓለም አኳያ ያለችበትን ደረጃ ማየት የሚያስችልና ልምድና ተሞክሮዎችን ለመለዋወጥ ምቹ ምህዳርን የሚፈጥር መሆኑን ጠቁመዋል፡፡
በየሁለት ዓመቱ በኦሎምፒክ መልክ የሚካሄድ የዓለም የክህሎት ወድድር መኖሩን የጠቆሙት ክብርት ሚኒስትር በዚህ መድረክ ዓለም አቀፍ ልምዶች የሚቀሰሙበት፣ የኢንዱስትሪ ትስስር የሚፈጠርበት እና የክህሎት ሽግግር የሚደርግበት በመሆኑ የተሻሉ ልምዶችን እንደሚገኙ አስረድተዋል፡፡
መረጃው የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር – ኢትዮጵያ / Ministry of Labor and Skills- Ethiopia ነው

Recent Comments