ኢንስቲትዩቱ ከቢሮው ጋር በ2017 በጀት ዓመት በቅንጅት ለመስራት ተፈራረመ፡፡
ቱሪዝም ማሰልጠኛ ኢንስቲትዩት ከአዲስ አበባ ባህል፣ ኪነ-ጥበብና ቱሪዝም ቢሮ ጋር በ2017 በጀት ዓመት በቅንጅታዊ አሰራር፣ ትብብርና ትስስር አብሮ ለመስራት የኢንስቲትዩቱ ም/ዋና ዳይሬክተር አቶ ሀብታሙ ክብረት እና የቢሮው ኃላፊ ሂሩት ካሳው(ዶ/ር) ተፈራረሙ፡፡
የጋራ ፊርማ ሥነ ሥርዓቱ በዓመቱ እስከ 2000 ለሚደርሱ የሆቴልና ቱሪዝም ሙያተኞች የሥራ ላይ ስልጠና ለመስጠት መሆኑን የገለጹት የኢንስቲትዩቱ የስልጠናና አቅም ግምባታ ዘርፍ ም/ዋና ዳይሬክተር አቶ ሀብታሙ ክብረት ይህ የከተማውን የቱሪዝም አገልግሎት ለማሻሻል እጅግ ጠቃሚ ነው ብለዋል፡፡
በከተማው እየተሰራ ካለው የቱሪዝም መሰረተ ልማት አንጻር የተሻለ አገልግሎት መስጠት ለሀገር ገጽታ ግንባታ መሠረት በመሆኑ ማሰልጠኛ ኢንስቲትቱ የተሰጠውን ተልዕኮ ለማሳካት እንደሚጠቅም አቶ ሀብታሙ ክብረት ገልጸዋል፡፡
የአዲስ አበባ ባህል ኪነጥበብ እና ቱሪዝም ቢሮ ኃላፊ ሂሩት ካሳው (ዶ/ር) በበኩላቸው በ2017 በጀት ዓመት ያቀድናቸውን ስራዎች ይበልጥ በተጠናከረ መልኩ ተንቀሳቅሰን በተሻለ ትብብርና ቅንጅት በመስራት አመርቂ ውጤት እናመጣለን ብለዋል።
ትክክለኛ መረጃዎችን ለማግኘት የሚከተሉትን ማስፈንጠሪያዎችን ይጠቀሙ
ፌስቡክ፡ https://www.facebook.com/tticommunication
ቴሌግራም ፡https://t.me/tticommunication
ዌብሳይት፡ https://www.tti.edu.et
Recent Comments