ታህሳስ 09 /2016 ዓ.ም የማሰልጠኛ ኢንስቲትዩቱ የሰልጣኞች መማክርት ጉባኤ የተቋሙ ዋና ዳይሬክተርን ጨምሮ ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች በተገኙበት ተቋቁሟል፡፡

የመማክርት ጉባኤው የስልጠና ጥራትን ለማስጠበቅና ሰልጣኞች የሚያጋጥማቸውን ችግሮች ለመፍታት በጋራ ሆኖ ለማስተካከል እንደሚያግዝ ተገልጿል ፡፡
ጉባኤው ዘጠኝ አባላት ያሉት ሲሆን ነጻ ሆነው የሚጠበቅባቸውን ኃላፊነት እንዲወጡ አስፈላጊው ድጋፍና እገዛ እንደሚደረግላቸው ተገልጾላቸዋል።፡