የኢትዮጵያ ቱሪስት አስጎብኝዎች ማህበር አባላት ለኢንስቲትዩቱ ቱሪዝም ሰልጣኞች ልምድ አካፈሉ፡፡
የኢትዮጵያ ቱሪስት አስጎብኚ ባለሙያዎች ማኅበር የዓለም አቀፍ ቱሪስት አስጎብኚ ባለሙያዎች ቀንን ምክኒያት በማድረግ ለቱሪዝም ማሰልጠኛ ኢንስቲትዩት ቱሪዝም ዘርፍ ሰልጣኞች ልምዳቸውን አካፍሏል፡፡
በሙያው የሚሰማሩ ተተኪው ትውልድ የተሻለ ቁመና እንዲኖራቸው በማሰብ በቱሪስት አስጎብኝነት ከፍተኛ ዕውቀት እና ልምድ ያካበቱ የማህበሩ አባላት ተሞክሯቸውን ማካፈላቸውን የገለጹት የማህበሩ ቦርድ አባልና የህዝብ ግንኙነት ኃላፊ አቶ ቢኒያም ሀይሉ በቀጣይነትም ከተቋሙ ጋር በመሆን ባለሙያዎች ተሞክሯቸውን በማካፈል ማህበራዊ ኃላፊነታችንን ለመወጣት እንሰራለን ብለዋል፡፡
በልምድ ልውውጡ ላይ ከተገኙት የኢንስቲትዩቱ ቱሪዝም ሰልጣኞች መካከል አያንቱ ዓለማየሁ የቱሪስት አስጎብኚነት ሙያ ሁልጊዜ ማገልገልና መማር ነው፣ ስለዚህ የቀደሙ ሙያተኞች በስራቸው ላይ ያጋጠማቸውን ችግሮችና ያለፉበትን ማካፈላቸው በቀጣይ ለሚሰማሩበት ሙያ እንዲዘጋጁ እንደሚረዳቸው ገልጻለች፡፡
ዓለም አቀፉ የቱሪስት አስጎብኚ ማኅበራት ፌዴሬሽን እ.ኤ.አ ከ1990 ጀምሮ በዓለም አቀፍ ዙርያ የቱሪስት አስጎብኚ ቀንን በየዓመቱ እ. ኤ. አ ፌብርዋሪ 21 እንደሚያከብር እና በአሁኑ ወቅት ከሰባ በላይ በሚሆኑ ሀገራት በየዓመቱ እየተከበረ እንደሚገኝ መረጃዎች ያመለክታሉ።
የዓለም አቀፉ የቱሪስት አስጎብኚ ማኅበራት ፌዴሬሽን አባል የሆነው የኢትዮጵያ ቱሪስት አስጎብኚ ባለሙያዎች ማኅበርም በልዩ ልዩ ዝግጅቶች ማክበሩ ተገልጿል፡፡
ትክክለኛ የኢንስቲትቱን መረጃዎችን ለማግኘት የኢንስቲትዩቱን
ፌስቡክ ገጽ https://www.facebook.com/tticommunication ወይም
ቴልግራም https://t.me/tticommunication
ዌብሳይት https://www.tti.edu.et/ ይጎብኙ
Ethiopian Tourist Guides Professional Association
Recent Comments