ቱ .ማ .ኢ የካቲት 13/2016 ዓ ም የቱሪዝም ማሰልጠኛ ኢንስቲትዩት አስተዳደር ሴት ሰራተኞች በሁለት ዙር ይሰጥ የነበረው የምግብ ዝግጅት ስልጠና ተጠናቀቀ።

በማጠቃለያው ፕሮግራም የተገኙት የተቋሙ የአመራርና አስተዳደር ዘርፍ ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ ገዛኸኝ አባተ እንደተናገሩት ይህ አይነት ስልጠና ሰራተኞች እራሳቸውን ወደ ኢንተርፕራይዝ እንዲያሳድጉ የሚረዳ መሆኑን በመጠቆም ሴት ሰራተኞች ተደራጅተው ይህን የምግብ ዝግጅት ፕሮግራም ለመስራት የሚያስችል በመሆኑ ተቋሙ በሚያስፈልገው ሁሉ እንደሚደግፍ ተናግረዋል ።
ይህንን ስልጠና ያዘጋጁት ስርዓተ ፆታ ዳይሬክቶሬት ክፍልና ስልጠናውን የሰጡ የተቋሙን አሰልጣኞች አመስግነዋል።
የተቋሙ ስርዓተ ፆታ ዳይሬክቶሬት ባለሙያ ወ/ሮ ንግስት ሲሳይ ይህን ስልጠና አቅደን እንዲሳካ ላደረጉት አመራሮችና ባለሙያዎች ምስጋና አቅርበው ሌሎች ስልጠናዎች እንደሚቀጥሉ ተናግረዋል።
ስልጠናውን ከተከታተሉት መካከል ወ/ሮ እፀገነት ታየ ስልጠናው በጣም ጠቃሚ እንደሆነና ያሰለጠኑ አሰልጣኞች በትዕግሥት ለማሳወቅ ብዙ ጥረት እንዳደረጉ ገልጸዋል።
ፕሮግራሙ ሰልጣኞች ያዘጋጁትን ኬክ በመቁረስ ተጠናቋል።