በእውቀትና በክህሎት ያደገ ማህበረሰብ ቴክኖሎጂ የመጠቀም እድሉ ይሰፋል፣ ተገልጋይን ያረካል።” አቶ ጌታቸው ነጋሽ
በእውቀትና በክህሎት ያደገ ማህበረሰብ ቴክኖሎጂ የመጠቀም እድሉ ይሰፋል፣ ተገልጋይን ያረካል። ይህን ያሉት የቱሪዝም ማሰልጠኛ ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር አቶ ጌታቸው ነጋሽ የኢስትሪፕ(EASTRIP) ፕሮጀክት የስድስት ወር የሥራ አፈፃፀም ሪፖርት መድረክን ሲከፍቱ ነው።
አቶ ጌታቸው እንዳሉት የስልጠና ተቋማት ሰጣኞቻቸውን በእውቀት እና በክህሎት የተካነ፣ በስነምግባሩ የተመረጠ፣ ብቁና ተወዳዳሪ የሆነ የሠው ኃይል ማፍራት ላይ አትኩረው መስራት ይጠበቅባቸዋል።
በዚህም ኢንስቲትዩቱን ኢስትሪፕ (EASTRIP) ፕሮጀክት በተቋሙ የሚሰጡ የሙያ ስልጠናዎች ደረጃቸውን የጠበቁ እና የገበያ ፍላጎትን መሠረት ያደረጉ እንዲሆኑ በጥናት የተደገፉ ሥራዎች እንድንሰራ እያገዘን ነው ብለዋል።
የኢስትሪፕ ፕሮጀክት የስድስት ወር አፈፃፀምን ሪፖርት የፕሮጀክቱ አስተባባሪ አቶ አብርሃም ለገሰ ለኢደስትሪ አማካሪ ቦርዱ እንዳቀረቡት በፕሮጀክት ከተያዙ እቅዶች ውስጥ ሥልጠና፣ ጥናትና ምርምር፣ ማማከር እንዲሁም በትብብር ስልጠና የተያዙ ሥራዎች ከእቅድ በላይ መሠራታቸውን ገልጸዋል።
በፕሮጀክት ተይዘው ያልተከናወኑ ያሏቸውን የህንፃ ግንባታ፣ የልምድ ልውውጥ የመሳሰሉት ደግሞ በሶስተኛው ሩብ ዓመት የተሻለ እንዲሆን የተጀመሩ ሥራዎች ተጠናክረው መሄድ እንዳለባቸው የቴክኒካል አማካሪ ቦርዱ አባላት ሃሳብ ሰጥተዋል።
በመጨረሻም የድሬደዋ ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ የፕሮጀክት አፈፃፀም ተሞክሮን የፕሮጀክቱ ክትትልና ግምገማ ስፔሺያሊስት አቶ መሣይ ለአማካሪ ቦርዱ አካፍለዋል።
ትክክለኛ የኢንስቲትዩቱን መረጃዎችን ለማግኘት
በፌስቡክ ገጽ https://www.facebook.com/tticommunication ወይም
ቴልግራም https://t.me/tticommunication
ዌብሳይት https://www.tti.edu.et/ ይጎብኙ
Recent Comments