ሰኔ 18/2015 ዓ.ም የቱሪዝም ማሰልጠኛ ኢንስቲትዩት ዓለም አቀፍ የትምህርት ጥራት ማረጋገጫ ስርዓትን ለመከተል የሚያስችል ቅድመ ዝግጅቱን አጠናቆ የሙከራ ትግበራ ሊጀምር መሆኑ ተገልጿል።

የኢንስቲትዩቱ የምርምርና ማማከር አገልግሎት ዘርፍ ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ ይታሰብ ሥዩም እንደገለፁት ከመጪው ሀምሌ 01/2015 በሁሉም የሥራ ክፍሎች የISO21001/2018 የሙከራ ትግበራ ይጀምራል ብለዋል። ይህ የሙከራ ትግበራ ከኢትዮጵያ ደረጃዎች ኢንስቲትዩት በተመደቡ ባለሙያዎችና ከየሥራ ክፍሉ በተመደቡ ባለሙያዎች የሰነድ ዝግጅቱ መጠናቀቁንም ጠቁመዋል፡፡
ስለሆነም ኢንስቲትዩቱ በ2016 በጀት ዓመት ሀገር አቀፍና እና ዓለም አቀፍ የጥራት ደረጃዎችን በሚያሟላ መልኩ ሰልጠና የሚሰጥ መሆኑን እና ይህም ተቋሙ በዓለም አቀፍ ደረጃ ተወዳዳሪ እንዲሆን እንደሚያስችለው አቶ ይታሰብ ሥዩም ተናግረዋል።
ለትግበራው ሥኬትም ሁሉም የተቋሙ ማህበረሰብ ዝግጁ እንዲሆን አሳስበዋል።
ከዚሁ ሂደት ጋር በተያያዘ የጥራት ደረጃውን ለማስጠበቅ የሚረዳ የቴክኖሎጂ ሽግግር ስልጠናም ለሰራተኞች ተሰጥቷል።
ስልጠናውን የተቋሙ አሰልጣኝ ቲጃኒ ሁሴን ሰጥተዋል፡፡