“ዜጎች ከቱሪዝም ዘርፍ የስራ ዕድል እንዲያገኙበት በትኩረት እየተሰራ ይገኛል” አቶ ገዛኸኝ አባተ
ቱሪዝም ማሰልጠኛ ኢንስቲት ከክልል ቱሪዝም ቢሮዎች፣ የስራና ክህሎት ቢሮዎችና በዘርፉ ስልጠና እየሰጡ ከሚገኙ ቴክኒክና ሙያ ተቋማት ጋር ስልጠናና ምክክር እያደረገ ይገኛል፡፡
በመርሃ ግብሩ ላይ የተገኙት የኢንስቲትዩቱ የስራ አመራርና አስተዳደር ዘርፍ ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ ገዛኸኝ አባተ እንደገለጹት ዜጎች ከቱሪዝም ዘርፍ የስራ ዕድል እንዲያገኙበት ኢንስቲትዩቱ ትኩረት ሰጥቶ እየሰራ እንደሚገኝ ተናግረዋል፡፡
በቅንጅት ከተሰራ በቂ የስራ እድል መፈጠር ይቻላል ያሉት ምክትል ዋና ዳይሬክተሩ አቶ ገዛኸኝ አባተ በምክክር መድረኩ የሚነሱ ሃሳቦች እና የሚቀርቡ ተሞክሮዎችን በመውሰድ በተደራጀ መልክ ሁሉም የበኩሉን ተሞክሮና ፈጠራ በመጨመር ከተሰራ ተጨባጭ ውጤት ማምጣት እንደሚቻል ገልጸዋል፡፡
በመጀመሪያ ቀን መርሐ ግብር የሀገራችን ቱሪዝም ያለበትን አጠቃላይ ሁኔታ የሚገልጽ ስልጠናና መወያያ ሰነድ የተዘጋጀ ሲሆን ከነዚህ መካከል “ሀላል ቱሪዝም” በሚል ርእስ በአሰልጣኝ ሰይድ የሱፍ ቀርቦ ውይይት ተደርጎበታል፡፡ ከዚህ በተጨማሪም ቱሪዝምና የስራ እድል እንዲሁም ኢኮ ቱሪዝምን የሚመለከቱ የስልጠናና መወያያ ርእሶች የሚቀጥሉ ይሆናል፡፡
ትክክለኛ መረጃዎችን ለማግኘት የሚከተሉትን ማስፈንጠሪያዎችን ይጠቀሙ
ፌስቡክ፡ https://www.facebook.com/tticommunication
ቴሌግራም ፡https://t.me/tticommunication
ዌብሳይት፡ https://www.tti.edu.et/

Recent Comments