“ቱሪዝም የስራ እድል መፍጠር ብቻ ሳይሆን ለሌሎች ስራ እድሎች መፈጠርም ምክንያት ይሆናል” አሰልጣኝ ፍሬው አበበ
ቱሪዝም ማሰልጠኛ ኢንስቲትዩት ከክልል ቱሪዝም ቢሮዎች፣ ከስራና ክህሎት ቢሮዎች እና ቴክኒክና ሙያ ተቋማት ጋር እተካሄደ በሚገኘው ምክክር መድረክ ቱሪዝም ለስራ እድል ያለው አስተዋጽኦ በሚል ርዕስ ስልጠና የሰጡት በኢንስቲትዩቱ የቱሪዝም አሰልጣኝ ፍሬው አበበ ቱሪዝም የስራ እድል መፍጠር ብቻ ሳይሆን ሌሎች ስራ እድሎች መፈጠርም ምክንያት ይሆናል ብለዋል፡፡ ይህን ውጤታማ ለማድረግ ለዘርፉ ተገቢ ትኩረት መስጠት ይገባል በዘርፉ የተሰማሩ አካላትም ጥሩ አገልግሎት መስጠት ይጠበቅባቸዋል ብለዋል፡፡
ከዚህ በተጨማሪም በመድረኩ ላይ “ኢኮ ቱሪዝም” በሚል ርእስ ኢኮ ቱሪዝም ለአንድ ሀገር ቱሪዝም እድገት፣ ለአካባቢ ጥበቃና ደህንነት ያለውን አስተዋጽኦ በሚመለከት በአሰልጣኝ አለምነህ መርሻ ቀርቦ ውይይት ተደርጎበታል፡፡
ትክክለኛ መረጃዎችን ለማግኘት የሚከተሉትን ማስፈንጠሪያዎችን ይጠቀሙ
ፌስቡክ፡ https://www.facebook.com/tticommunication
ቴሌግራም ፡https://t.me/tticommunication
ዌብሳይት፡ https://www.tti.edu.et/
Recent Comments