ቱሪዝም ማሰልጠኛ ኢንስቲትዩት ከክልል ቢሮዎችና ኮሌጆች ጋር በመቀናጀት የተሰሩ የዘጠኝ ወር አፈጻጸም ቀረበ ፡፡
ቱሪዝም ማሰልጠኛ ኢንስቲትዩት ባለፉት ዘጠኝ ወራት ከክልል ቱሪዝም ቢሮዎች፣ ሥራና ክህሎት ቢሮዎች እና ቴክኒክና ሙያ ተቋማት ጋር በመሆን የሰራቸው የዘጠኝ ወር አፈጻጸም ተገመገመ፡፡
ባለፉት ዘጠኝ ወራት ከሶስት ሺህ ሁለት መቶ በላይ ለሚሆኑ የዘርፉ ባለሙያዎችና መምህራን ተግባርን መሰረት ያደረጉ ልዩ ልዩ ስልጠናዎች መሰጠታቸውን የአጫጭርና የማታ ትምህርት ክፍል ኃላፊ አቶ ግርማ ደቀባ ገልጸዋል፡፡
ተቋሙ በዘርፉ የሚታየውን የሰው ሀይል እጥረት ለመቅረፍና በተለይም ስለ ዘርፉ የሚታዩ የግንዛቤ ችግሮችን ለመፍታት እየሰራ የሚገኘው አበረታች መሆኑን ተሳታፊዎች ገልጸዋል፡፡
ኢንስቲትዩቱ አብሮ እየሰራ ከሚገኙ ቴክኒክና ሙያ ተቋማት መካከል ጭዳ ኢንዱስትሪያል ኮሌጅ፣ ቅዱስ ላልይበላ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ፣ ደብረብርሃን ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ እና አርባምንጭ ቴክኒክና ሙያ ኮሌጅ የነበራቸውን መልካም ተሞክሮ አቅርበዋል፡፡
የስልጠናና አቅም ግንባታ ዘርፍ ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ ሀብታሙ ክብረት እንደገለጹት በዚህ ዘርፍ የሚታየውን የሰለጠነ የሰው ሀይል እጥረት ለመቅረፍ የቴክኒክና ሙያ ተቋማት በአጫጭር ጊዜ ስልጠናዎች ላይ ትኩረት ማድረግ ይገባል ብለዋል፡፡
የተቋሙ ሥራ አመራርና አስተዳደር ዘርፍ ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ ገዛኸኝ አባተ በበኩላቸው የተጀመረውን ቅንጅታዊ አሰራር በማጠናከር፣ ባለው ሀብት በመስራት በቀጣይ ውጤት የተሻለ ውጤት ማምጣት እንደሚገባ አሳስበዋል።
ትክክለኛ መረጃዎችን ለማግኘት የሚከተሉትን ማስፈንጠሪያዎችን ይጠቀሙ
ፌስቡክ፡ https://www.facebook.com/tticommunication
ቴሌግራም ፡https://t.me/tticommunication
ዌብሳይት፡ https://www.tti.edu.et/
Recent Comments