የቱሪዝም ዘርፍ ሙያ መስኮችና እድሎች ላይ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ተሰጠ።

ቱሪዝም ማሰልጠኛ ኢንስቲትዩት በዘርፉ ያለውን ሙያና የስራ እድሎችን በሚመለከት ከንፋስ ስልክ ላፍቶ ክ/ከተማ ወረዳ ስድስት ለተወጣጡ አንድ መቶ ሀምሳ ሴቶች ስልጠና ሰጠ።
የስልጠና መድረኩን ያስጀመሩት የጥናት ምርምር እና ማማከር ዘርፍ ም/ዋና ዳይሬክተር አቶ ይታሰብ ስዩም ተቋሙ በያዘው የማህበረሰብ አቀፍ አገልግሎት ዕቅድ መሰረት በተለይም ሴቶች በዘርፋ የአጫጭር ጊዜ ስልጠናዎችን በመውሰድ የራሳቸውን ስራ ዕድል እንዲፈጥሩ ለማስቻል መሆኑን ገልፀዋል። ኢንስቲትዩቱ በወሰዱት ስልጠና መሰረት በሚመርጡት የሙያ መስክ ላይ በቀጣይ የአጭር ጊዜ ስልጠና እንደሚሰጥም ተገልጿል።
ስለ ዘርፋ የግንዛቤ ስልጠና የወሰዱት ተሳታፊዎችም በቀጣይ ሊሰለጥኑበት የሚፈልጉትን የሙያ መስክ መርጠዋል።
የግንዛቤ ማስጨበጫ ስለጠናውን ከፍተኛ የቱሪዝም ዘርፍ አሰልጣኝ ተፈሪ አቡሃይ ሰጥቷል።
ትክክለኛ መረጃዎችን ለማግኘት የሚከተሉትን ማስፈንጠሪያዎችን ይጠቀሙ
ፌስቡክ፡ https://www.facebook.com/tticommunication
ቴሌግራም ፡https://t.me/tticommunication
ዌብሳይት፡ https://www.tti.edu.et/