ሀገር አቀሀገር አቀፍ የጥናትና ምርምር ኮንፍረንስ ተካሄደ፡፡
ቱሪዝም ማሰልጠኛ ኢንስቲትዩት 13ኛውን ሀገር አቀፍ የጥናትና ምርምር ኮንፍረንስ “ዘላቂነት ያለው የቱሪዝም ልማትን ማረጋገጥ” በሚል መሪ ቃል አካሄደ፡፡
የጥናትና ምርምር ኮንፍረንሱ ላይ የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴኤታ ዶ/ር ተሻለ በሬቻ በጥናትና ምርምር የሚደገፍ ሥራ ውጤታማ ይሆናል ብለዋል፡፡ ማሰልጠኛ ኢንስቲትዩቱ ከዚህ በፊት ያካሄዳቸው የጥናትና ምርምር ስራዎች ለመንግስት ፖሊሲ ግብዓት የሚጠቅሙ መሆኑን የገለጹት ዶክተር ተሻለ በሬቻ እያካሄደ የሚገኘው የጥናት ውጤቶች የተሰጡትን ተልኮዎች በላቀ ደረጃ ለመወጣት እያስቻለው ይገኛል ብለዋል፡፡
በተለይ በሀገራችን ያለውን የሥራ ገበያ አለመጣጣም መፍትሔ ለመስጠት የሚካሄዱ ጥናቶችና እና ከባለድርሻ አካላት ጋር መሥራት አስፈላጊ እንደሆነም ሚኒስትር ዴኤታው ገልጸዋል፡፡
በኮንፍረንሱ ላይ ቁልፍ መልዕክት ያስተላለፉት የቱሪዝም ሚኒስቴር ሚኒስትር ደኤታ አቶ ስለሺ ግርማ በሀገራችን የዘላቂ ቱሪዝም ፍኖተ ካርታ እየተዘጋጀ መሆኑን ገልጸው ሀገራችን ያላትን የቱሪዝም ጸጋ በዘላቂነት ለመጠቀም የሚያስችሉ ስትራቴጂዎችን መከተል፣ መዳረሻዎችን በዘላቂነት መንከባከብ ያስፈልጋል ብለዋል፡፡
የኢንስቲትዩቱ ዋና ዳይሬክተር አቶ ጌታቸው ነጋሽ በበኩላቸው ማሰልጠኛ ኢንስቲትዩቱ ከተሰጡት ተልዕኮዎች መካከል የጥናትና ምርምር ሲያካሂድ በዘርፉ የሚታዩ ችግሮችን ለመፍታት፣ ተቋሙ የሚሰጠውን አገልግሎት ለማሻሻልና ስለዘርፉ ተጨማሪ እውቀቶችን ለማዳበር መሆኑን ገልጸዋል፡፡
በዕለቱ ማህበረሰብ አቀፍ አገልግሎት፣ የቅርሶች አስተዳደርና ጥበቃ፣ሀገር በቀል እውቀቶች እና የቱሪዝም ማርኬቲግ የሚመለከቱ ጥናታዊ ጽሁፎች ቀርበዋል፡፡

Recent Comments