ኢንስቲትዩቱ ተጨማሪ ገቢ ለማመንጨት የሚያስችል እንተርፕራይዝ አቋቋመ፡፡

ቱሪዝም ማሰልጠኛ ኢንስቲትዩት የሚሰጠውን ስልጠና የሚደግፍና ተቋሙ ምርትና አገልግሎትን በማቅረብ ተጨማሪ ገቢ ለማመንጨት የሚያስችል እንተርፕራይዝ መቋቋሙን የኢንስቲትዩቱ ዋና ዳይሬክተሩ አቶ ጌታቸው ነጋሽ ገልጸዋል፡፡
አዲሱ የትምህርትና ስልጠና ፖሊሲ ውጤት ተኮር ስልጠናዎችን በመስጠት ቴክኖሎጂዎችን የመስራትና ሀብት መፍጠርን የሚደግፍ መሆኑን ያስታወሱት አቶ ጌታቸው ነጋሽ የኢንተርፕራይዙ መቋቋም የተቋሙ ሰራተኞችና ሰልጣኞች ከተቀጣሪነት ይልቅ የስራና ሀብት ፈጣሪነትን እሳቤ እንዲይዙ ያደርጋል ብለዋል፡፡
“ድንቅነሽ የቱሪዝም ልማት ኢንተርፕራይዝ” የሚል ስያሜ ያለው መሆኑን የገለጹት ዋና ዳይሬክተሩ በኢንስቲትዩቱ ሜክሲኮ ግቢ ስራ እንዲጀምር ቅድመ ዝግጅቶች እየተጠናቀቁ መሆኑን ገልጸዋል፡፡
በመንግስት በጀት መሸፈን የማይቻሉ ወጪዎችን ተቋሙ በራሱ እንዲያስፈጽም የሚያግዝ በመሆኑ ከፍተኛ ትኩረት ሊሰጠው ይገባል ያሉት የተቋሙ የጥናትና ምርምር እና ማማከር አገልግሎት ዘርፍ ም/ዋና ዳይሬክተር አቶ ይታሰብ ሥዩም ለስልጠና የሚያገለግል የሃሳብ ማመንጫ እና ማበልጸጊያ (incubation center) ጎን ለጎን አብሮ እንደሚቋቋም ገልጸዋል። ይህ ዕቅድ እንዲሳካ ሁሉም ኢንስቲትዩቱ ማህበረሰብ የበኩሉን አስተዋጽኦ እንዲያደርግ አሳስበዋል፡፡
እንተርፕራይዙ በዳቦና ኬክ ዝግጅት፣ በምግብ ዝግጅት እና ላውንደሪ አገልግሎት ዘርፍ ስራ የሚጀምር መሆኑ ታውቋል።
በዕለቱ የእንተርፕራይዙ ስራ አስኪያጅ አቶ መለሰ ወርቁ እና የቦርድ አባላት ከማኔጅመንት አባላት ጋር ትውውቅና ውይይት አካሂዷል፡፡
ትክክለኛ መረጃ ለማግኘት የሚከተሉትን ሊንክ በመጠቀም የፌስቡክ ገጻችን ይጎብኙ፣ ላይክ፣ ሼር ያድርጉ
We kindly invite you to join our telegram group https://t.me/tticommunication and like, follow, and share the Facebook page https://www.facebook.com/tticommunication