በቱሪዝም ዘርፍ የተሰሩ ሀገር አቀፍ ፕሮጀክቶችን የሚደግፍ ስልጠና ሊሰጥ ነው።
የቱሪዝም ማሰልጠኛ ኢንስቲትዩት ሀገር አቀፍ ፕሮጀክቶችን በቱሪዝምና በሆቴል ዘርፍ በሰለጠነ የሰው ሀይል ለመሙላት የሚያስችል ስልጠና ለመስጠት ዝግጅቱ መጠናቀቁን የተቋሙ ዋና ዳሬክተር አቶ ጌታቸው ነጋሽ ተናግረዋል፡፡
የዚሁ ፕሮጀክት አካል የሆነው የወንጪ ሀይቅ መዳረሻ ዙሪያ ለመነጋገር የተቋሙ ኃላፊዎች ከኦሮሚያ ክልል ምዕራብ ሸዋ ዞን ከሚገኙ የቴክኒክና ሙያ ኮሌጀ ዲኖችና ከክልል ባህል ቱሪዝም ቢሮ ኃላፊዎች ጋር ውይይት አድርገዋል።
በውይይቱ በዘርፉ ሥራ ላይ እና ከሥራ ውጪ ያሉ ወጣቶችን በቱሪዝምና በሆቴል መስክ እንዲሁም ሙያው ከሚፈልገው ስነምግባር ዙሪያ ስልጠና በመስጠት በቱሪስት መዳረሻው የሚመጡትን ቱሪስቶች መያዝ የሚያስችል ስልጠና መስጠት አስፈላጊ መሆኑ ተገልጿል።
ስለሆነም ለሥልጠናው ሌሎች ባለድርሻ አካላትን ፣ የአከባቢውን ማህበረሰብ በማሳተፍ መሰራት እንደለበት ስምምነት ላይ ደርሰዋል።
ከወንጪ ፣ ወሊሶና አምቦ የመጡ የሥራ ኃላፊዎች እንደተናገሩት ተቋሙ የሥራው ባለቤት አድርጎ እኛን በመጥራት ለወጣቶች በቱሪዝምና በሆቴል ዘርፍ ስልጠና ለመስጠት ማቀዱ መልካም መሆኑን በመግለጽ ከራሳቸው የሚጠበቅባቸውን ለመወጣት ቃል ገብተዋል፡፡
ኢንስቲትዩቱ ከዚህ ቀደም በደብረብርሃን እና በኮንታ ዞን በቱሪዝምና በሆቴል ዘርፍ በመስተንግዶ ዙሪያ ስልጠና መስጠቱ ይታወቃል፡፡
ትክክለኛ መረጃዎችን ለማግኘት የሚከተሉትን ማስፈንጠሪያዎችን ይጠቀሙ
ፌስቡክ፡ https://www.facebook.com/tticommunication
ቴሌግራም ፡https://t.me/tticommunication
ዌብሳይት፡ https://www.tti.edu.et/
Recent Comments