EASTRIP ፕሮጀክት ተቋሙን የሥልጠናና የምርምር ሥራዎች እየደገፈ መሆኑ ተገለጸ።

EASTRIP ፕሮጀክት ተቋሙን የሥልጠናና የምርምር ሥራዎች እየደገፈ መሆኑን የፕሮጀክቱ አስተባባሪ አቶ አብርሃም ለገሰ የአራት ወር የሥራ አፈፃፀም ለሠራተኛው ባቀረቡበት ወቅት ተናግረዋል።
የፕሮጀክቱ የፋይናንስ አፈፃፀም በጥሩ እየተመራ በመሆኑ ቀጣይ ሥራዎችም በትኩረትና በጥብቅ ክትትል እንዲፈጸሙ የኢንስቲትዩቱ ዋና ዳይሬክተር አቶ ጌታቸው ነጋሽ የሥራ መመሪያ ሰጥተዋል።
የቀጣይ የስድስት ወር ሥራዎችን ዕቅድ መከለስ የሚያስፈልጋቸውን በመከለስ ሥራዎች በተያዘላቸው ጊዜ እንዲከናወኑ በማሳሰብ የፕሮግራም ማጠቃለያ ተደርጓል።
ትክክለኛ መረጃዎችን ለማግኘት የሚከተሉትን ማስፈንጠሪያዎችን ይጠቀሙ
ቴሌግራም ፡https://t.me/tticommunication
ዌብሳይት፡ https://www.tti.edu.et/