ቱሪዝም ማሰልጠኛ ኢንስቲትዩት17ኛውን የሰንደቅ ዓላማ ቀን አከበረ።
የቱሪዝም ማሰልጠኛ ኢንስቲትዩት አመራር ፣ሰራተኞችና ሰልጣኞች በተገኙበት በሀገር አቀፍ ደረጃ የሚከበረውን የሰንደቅ ዓላማ ቀን “ሰንደቅ ዓላማችን ለብሔራዊ አንድነታችን፣ ለሉዓላዊነታችንና ለኢትዮጵያ ከፍታ “በሚል መሪ ቃል አከበሩ።
እለቱን አስመልክቶ መልዕክት ያስተላለፉት የኢንስቲትዩቱ ዋና ዳይሬክተር አቶ ጌታቸው ነጋሽ ሰንደቅ ዓላማችን የአባቶቻችን እና እናቶቻችን ገድል፣የነጻነት ፣የሉዓላዊነት የመስዋዕትነት እንዲሁም የብዝሃነታችን መገለጫ መሆኑን ገልጸው የሰንደቅ ዓላማ ቀን በዓመት አንድ ይከበራል፤ ይሁን እንጂ ሰንደቅ ዓላማ ሁል ጊዜ ከኛ ጋር የሚኖር ልናከብረውና ልንጠብቀው የሚገባ ነው ብለዋል፡፡
የኢንስቲትዩቱ ማህበረሰብ በተለይ ወጣት ሰልጣኞች ይህን ሰንደቅ ዓላማ ስናከብር በትውልድ ቅብብሎሽ ሉዓላዊነታችንን ጠብቀን lዛሬ ለማቆየት የተከፈለውን መስዋዕትነት እና ህብረብሔራዊ አንድነታችን የሚገለጽበት መሆኑን በመገንዘብ ለሰንደቅ አላማ ተገቢውን ክብር እንዲሰጡም አሳስበዋል።
” ሰንደቅ ዓላማችን ለብሔራዊ አንድነታችን፣ ለሉዓላዊነታችንና ለኢትዮጵያ ከፍታ ”
ትክክለኛ መረጃዎችን ለማግኘት የሚከተሉትን ማስፈንጠሪያዎችን ይጠቀሙ
ፌስቡክ፡ https://www.facebook.com/tticommunication
ቴሌግራም ፡https://t.me/tticommunication
ዌብሳይት፡ https://www.tti.edu.et/
Recent Comments