ኢንስቲትዩቱ የሀገራችንን ቱሪዝምና ሆስፒታሊቲ ኢንዱስትሪ እድገት ለማፋጠን የሚያግዝ የጥናትና ምርምር ኮንፍረንስ እየተካሄደ ይገኛል።

በቱሪዝም ማሰልጠኛ ኢንስቲትዩት አዘጋጅነት የቱሪዝምና ሆስፒታሊቲ ዘርፋን እድገት ለማሻሻልና ተቋሙ የሚሰጣቸውን አገልግሎት ጥራት ለማስጠበቅ የሚያግዝ ለአንድ ቀን የሚቆይ የጥናትና ምርምር ኮንፍረንስ መካሄድ ጀምሯል።
ኮንፍረንሱን ያስጀመሩት የኢንስቲትዩቱ ዋና ዳይሬክተር አቶ ጌታቸው ነጋሽ የተዘጋጁት የጥናት ምርምር ሥራዎች ዘርፋን ለማሳደግና ኢንስቲትዩቱ የሚሰጠውን የስልጠና እና የማማከር አገልግሎቶች ጥራት ለማስጠበቅ ትልቅ አቅም ይሆናል ብለዋል።
አሁን ባለንበት ወቅት በሀገራችን የሥራ አጥነት ችግር መኖሩንና በቱሪዝምና መስተንግዶ ዘርፍ ደግሞ ያለው የሰለጠነ የሰው ሀይል እጥረት መኖሩን የተቋሙ ጥናት የሚያመላክት መሆኑን የገለፁት ዋና ዳይሬክተሩ አቶ ጌታቸው ነጋሽ እንደዚህ አይነት ችግሮችን ለመፍታት በተቋሙ ምሁራን እየተሰሩ የሚገኙ የጥናትና ምርምር ስራዎች ለፖሊሲ አውጭዎች ግብዓት ስለሚሆኑ ጥናቶቹ አገልግሎት ላይ እንዲውሉ ክትትል ይደረጋል ብለዋል።
በጥዋቱ የመጀመሪያ መርሐግብር የቱሪዝም ንግድ ትስስር ለስራ ዕድል ፈጠራ ያለውን አስተዋጽኦ በአሰልጣኝ ሳህለ ተከሌ እና የኢኮ ቱሪዝም አቅም በዳውሮ ዞን በሚል ርዕስ አሰልጣኝ አህደር ጠና ቀርቧል። መድረኩን በአወያይነት የአዲስ አበባ ዩንቨርሲቲ ተባባሪ ፕሮፌሰር ዶ/ር ተስፋዬ ዘለቀ እየመሩ ነው።
ትክክለኛ መረጃ ለማግኘት የሚከተሉትን ሊንክ በመጠቀም የፌስቡክ ገጻችን ይጎብኙ፣ ላይክ፣ ሼር ያድርጉ
We kindly invite you to join our telegram group https://t.me/tticommunication and like, follow, and share the Facebook page https://www.facebook.com/tticommunication