ቱሪዝም ማሰልጠኛ ኢንስቲትዩት ዓለም አቀፍ የትምህርት ጥራት ደረጃን ለማስጠበቅ የወጣውን ISO21001-2018 ትግበራ ጀምሯል።

የማሰልጠኛ ኢንስቲትዩቱ የሶስት ወራት ዕቅድ አፈጻጸም በመልካም አስተዳደር ፣ በISO21001-2018 እና የታቀዱ ስራዎች አፈጻጸምን ገምግሟል።
የተቋሙ የስራ አፈጻጸምና ጥራት ደረጃውን ተፈጻሚ ለማድረግ የተደረገው ዝግጅት ተቋሙ የዓለም አቀፉ የትምህርት ጥራት ስርዓትን ለመተግበር የሚያችል መሆኑን የገለጹት የኢንስቲትዩቱ ዋና ዳይሬክተር አቶ ጌታቸው ነጋሽ ኢንስቲትዩቱ የጥራት ደረጃውን የምስክር ወረቀት አግኝቶ ደረጃውን የጠበቀ አገልግሎት እንዲሰጥ ሁሉም ሰራተኛ የበኩሉን መወጣት ይጠበቅባቸዋል ብለዋል።
የ2016 በጀት ዓመት የሶስት ወራት ዕቅድ አፈጻጸም በአቶ ተመስገን በቀለ ቀርቦ ውይይት የተደረገበት ሲሆን በበጀት ዓመቱ ሊሰሩ ከታቀዱ ሥራዎች አብዛኛዎቹ ከእቅድ በላይ መሠራታቸው እንደ ጠንካራ ጎን ተወስዷል።
የመልካም አስተዳደር አፈጻጸም በለውጥና መልካም አስተዳደር ዳይሬክተር አቶ ተስፋአገኘሁ ለገሰ ሪፖርት የተደረገ ሲሆን ከሰራተኛውና ከባለድርሻ አካላት የተሰባሰቡ የመልካም አስተዳደር ችግር ሆነው የቀረቡ ጉዳዮች ተለይተው ቀርበዋል።ለማሻሻልም ሁሉም በቁርጠኝነት ኃላፊነት እንዳለበት በውይይቱ ተገልጿል።
የISO21001-2018 ያለበትን ደረጃና የወደፊት አቅጣጫ በአቶ ሀማሴን ሀድገምበስ ቀርቦ አስተያየት ተሰጥቶበታል።
በመጨረሻም የተቋሙ ዋና ዳይሬክተር ከሠራተኛዉ ለቀረቡ ጥያቄዎችንና አስተያየቶችን ምላሽ በመስጠት የማጠቃለያና ቀጣይ ትኩረት የሚሹ ጉዳዮችን በመግለጽ የሥራ አቅጣጫ ሰጥተዋል።
ትክክለኛ መረጃ ለማግኘት የሚከተሉትን ሊንክ በመጠቀም የፌስቡክ ገጻችን ይጎብኙ፣ ላይክ፣ ሼር ያድርጉ