ለሆቴሎችና አስጎብኚ ድርጅቶች የማማከር አገልግሎት እየተሰጠ ነው።

ቱሪዝም ማሰልጠኛ ኢንስቲትዩት በአራት ከተሞች ማለትም በመቀሌ ፣በአክሱም፣ በአዳማ እና ቢሾፍቱ ከተሞች በሚገኙ ሆቴሎችና ሪዞርቶች እንዲሁም አስጎብኚ ድርጅቶች የማማከር አገልግሎት እየተሰጠ ነው።
የተቋሙ የማማከር እና ማርኬቲንግ ዴስክ ኃላፊ አቶ ታምራት ተፈራ እንደገለፁት ተቋሙ ከተሰጠው ተለዕኮ አንዱ የማማከር ሙያዊ ድጋፍ በመሆኑ ከአሰልጣኞች እና ከዘርፉ ባለሙያዎች ጋር በመቀናጀት በተለያዩ ከተሞች በሚገኙ ሆቴሎች እና አስጎብኚ ድርጅቶች የማማከር አገልግሎት እየተሰጠ እንደሆነ ገልጸዋል።
በዛሬው እለት በተለያዪ ከተሞችና ሆቴሎች የማማከር አገልግሎት የተሰጠባቸው በመስተንግዶ ፣እንግዳ አቀባባልእና የምግብ ዝግጅቶች ዙሪያ የሚታዪ ክፍተቶችን እንዲያሟሉ እና መልካም ተሞክሮዎች እንዲቀጥሉ አስተያየት ተሰጥቷል።
በአዳማ ከተማ ራስ አዳማ ሆቴል ኦፕሬሽን ሥራ አስኪያጅ አቶ ጌትነት እና አዳማ ጀርመን ሆቴል ሥራአስኪያጅ አቶ ለገሰ ንጉሱ በተመሳሳይ ለሆቴሎቻቸው በዘርፉ የሰለጠነ የሰው ሀይል ማጣት እና የሰለጠኑት ባለሙያዎችም አንድ ቦታ ረግቶ አለመሥራት ችግሮች እንዳሉ ተገልጿል።
በተጨማሪም ኢንስቲትዩቱ በየጊዜው የሚያደርጓቸው የተግባር ላይ ስልጠና እና የማማከር አገልግሎት መቀጠል እንዳለበት ሲሉ አሳስበዋል። ይህ የማማከር አገልግሎት በሁሉም ከተሞች ባሉ ሆቴሎችና አስጎብኚ ድርጅቶች እንደሚቀጥልም ተገልጿል ።
ትክክለኛ መረጃዎችን ለማግኘት የሚከተሉትን ማስፈንጠሪያዎችን ይጠቀሙ
ፌስቡክ፡ https://www.facebook.com/tticommunication
ቴሌግራም ፡https://t.me/tticommunication
ዌብሳይት፡ https://www.tti.edu.et/