ኢንስቲትዩቱና በማዕከላዊ ኢትዮጵያ የሚገኘውን የቱሪዝም ሀብት ተጠቃሚነትን ለማሳደግ እየተሰራ መሆኑ ተገለጸ።

ቱሪዝም ማሰልጠኛ ኢንስቲትዩት በዘርፉ የሆቴልና ቱሪዝም ሙያ ስልጠናዎችን በመስጠት ባለፈ ችግር ፈቺ የሆኑ የጥናትና ምርምር ስራዎችን እያካሄደ ነው። ኢንስቲትዩቱ ከማዕከላዊ ኢትዮጵያ ባህልና ቱሪዝም ቢሮ ጋር በመተባበር የክልሉን እምቅ የቱሪዝም ሀብት ተጠቃሚነትን ለማሳደግ በርካታ ተግባራት እየተከናወኑ እንደሚገኝ የኢንስቲትዩቱ የጥናትና ምርምር እና ማማከር ዘርፍ ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ ይታሰብ ሥዩም ገልጸዋል።
ማዕከላዊ ኢትዮጵያ በቅርብ ዓመት እራሳቸውን ችለው ከተደራጁ ክልሎች መካከል አንዱ ሲሆን በዓለም ቅርስነት ከተመዘገቡት መካከል የጥያ ትክል ድንጋይ፣ መልካ ቁንጡሬ እንዲሁም ለሀይማኖታዊና ሀገር ውስጥ ቱሪዝም መሆን ከሚችሉት እንደ ምድረከብድ፣ አዳዲ ማሪያም፣ ተፈጥሮን ለማድነቅ የሚሆን እንደ ሀረ ሸይጣንና የመሳሰሉ የቱሪስት መስህቦች መገኛ ነው።
ኢንስቲትዩቱ እየሰራቸው ከሚገኙ ስራዎች መካከል በክልሉ የሚገኙ የቱሪዝም ሀብቶችና ተግዳሮቶች ላይ ያተኮረ ጥናት መካሄዱን የገለጹት አቶ ይታሰብ ጥናቱን መሰረት በማድረግ የቱሪስት ማፕ የተዘጋጀ ሲሆን አንድ ቱሪስት ወደ ክልሉ ቢሄድ ከየት እስከ የት ምን ጎብኝቶ መመለስ እንደሚችል የሚገልገልጽ የቱር ፓኬጅ ሰነድም ተዘጋጅቷል ብለዋል።
እነዚህ ተዘጋጅተው የተጠናቀቁ ሰነዶችን ክልሉ በሚያዘጋጀው መርሃግብር ላይ ርክክብ ይደረጋል ያሉት አቶ ይታሰብ ከዓለም ባንክ EASTRIP ፕሮጀክት ጋር በመተባበር የተለያዩ ዞኖች ሀገር በቀል የባህል ምግብ ዝግጅት እውቀቶች ምርምር ተደርጓል ብለዋል።
ከዚያ መካከል የዳውሮ፣ ወላይታ፣ ሀዲያ ፣ ስልጤ እና በቅርቡ የተሰራው የየም ባህላዊ ምግቦች ተጠቃሸ እንደሆኑ ገልፀዋል። የጥናት ቡድኑ የሚዘጋጁ የባህል ምግቦች የሚዘጋጁበትን ግብዓቶች ዝርዝር ሳይንሳዊ በመሆነ መለኪያ ዘዴ በመጠቀም ከሚያዘጋጁት እናቶች ጋር በመሆን ተገቢውን መረጃ በመውሰድ የምግብ ጥሬ እቃ ዝርዝርና መጠን (ሪሲፒ) ያዘጋጁሉ፡፡
ኢትዮጵያ ለተለያዩ ቱሪዝም አይነቶች የሚሆኑ በቂ የቱሪዝም ሀብት ባለቤት ናት። በተለይ እንደ ኢትዮጵያ ባሉ ሰፊ ባህልና የምግብ አሰራር ባለባቸው ሀገራት የምግብ ቱሪዝምን ለማስፋፋት የሚያስችል ዕምቅ ሀብት አለ፤ ይሁንና ይህንን የቱሪዝም ዘርፍ ምን ያክል ጥቅም ላይ ውሏል ተብሎ ሲጠየቅ እምብዛም ያልተጠቀምንበት መሆኑን የሚገልጹ ምሁራን በርካታ ናቸው። በዓለም ላይ የምግብ ቱሪዝም በየዓመቱ ከሰባት እስከ 12 በመቶ እድገት እያሳየ ትልቅ ትኩረት እየተሰጠው ያለ የቱሪዝም ዘርፍ መሆኑን መረጃዎች ያሳያሉ፡፡
እንደ ምክትል ዋና ዳይሬክተሩ ገለጻ እነዚህን የባህል ምግቦች ምርምር ማካሄድና መሰነድ ይገባል ይላሉ፡፡ እውቀት በጽሁፍ ካልተቀመጠ ሊረሳ፣ ሊበረዝ ይችላል ፤ የወጭ ሀገር ምግቦች ብቻ ናፋቂ እንዳንሆን የራሳችንን እውቀት ይዘን እዛ ላይ ተጨማሪ ነገሮችን መስራት ይቻላል ፣ ይህ እውቀቱም ለትውልድ ለማሸጋገር ይረዳል ብለዋል፡፡
የባህል ምግቦች የዕሴት ሰንሰለታቸው ሰፊ ነው ፣ ትውልዱ በራሱ ሀብት አየኮራ ሥራ እድልን በመፍጠር የኢኮኖሚ ተጠቃሚ እንዲሆኑ ማድረግ፡፡የሀገራችን ባህላዊ ምግቦች ተፈጥሯዊ (ኦርጋኒክ) ግብዓቶችን በመጠቀም የሚዘጋጁ በመሆናቸው በጣዕማቸው ቶሎ የሚወደዱ ስለሆነ ለምግብ ቱሪዝም (gastronomy tourism) ትልቅ መሰረት እንደሚሆን ገልጸዋል፡፡
እነዚህ ጥናት የተሰራባቸው የባህል ምግቦች በመጀመሪያ ዙር የተዘጋጁት ለሆቴሎች ተደራሽ እየተደረጉ መሆኑን የገለጹት ም/ዋና ዳይሬክተሩ አሁን በማዕከላዊ ኢትዮጵያ የተሰሩ ምግቦች እንደ መጀመሪያው ዙር ሆቴሎች በምግብ ዝርዝራቸው ውስጥ አስገብቶ አገልግሎት እንዲሰጡበት ይደረጋል ብለዋል፡፡
ይህን ጥናት ማካሄድ እንደ ክልሉም ሆነ አንደ ሀገር እንደ አንድ የሥልጠና መሳሪያ ልንጠቀምበት እንችላለን ያሉት ም/ዋና ዳይሬክተሩ በተለይ ይህን ጥናት ተቀብሎ በሆቴሎቻቸው ውስጥ አገልግሎት እየሰጡበት የሚገኙ ሆቴሎች ኢኮኖሚያዊ ጠቀሜታ የያለው ዘርፈ ብዙ ጥቅሞችን የሚሰጥ እንደሆነ ገልጸዋል::
አንድ ጎብኚ ኪሚኖርበት ሥፍራ ወደ ሌላ ቦታ ለመሄድ ከሚመርጣቸው ነገሮች አንዱ ምግብ እንደ መሆኑ እንደ ሀገርም ብዙ ዓይነት የብሔር ብሔረሰቦች ምግቦች ያሉን በመሆኑ ባህላዊ ምግቦቻችን ላይ እና የምግብ ቱሪዝም ከፍተኛ ትኩረት ሊሰጠው የሚገባ ነው ይላሉ፡፡
ቱሪዝም ማሰልጠኛ ኢንስቲትዩት ባህላዊ ምግቦችና የቱሪስት መዳረሻ ሥፍራዎች እንዲታወቁ ግንዛቤ በመፍጠር፣ ጥናቶችን በማካሄድ ፣የቱሪዝም ሀብቶች እንዲታወቁ በማድረግና ሌሎችንም ተግባራት በማከናወን የበኩሉን አስተዋጽኦ እያደረገ እንደሚገኝ አቶ ይታሰብ ሥዩም ገልጸዋል፡፡
ትክክለኛ መረጃዎችን ለማግኘት የሚከተሉትን ማስፈንጠሪያዎችን ይጠቀሙ
ፌስቡክ፡ https://www.facebook.com/tticommunication
ቴሌግራም ፡https://t.me/tticommunication
ዌብሳይት፡ https://www.tti.edu.et/