ቱሪዝም ማሰልጠኛ ኢንስቲትዩት ተጠሪ ሆኖ በአዲስ መልክ ከተዋቀረው የሥራና ክህሎት ሚኒስትር ጋር ትውውቅ አደረገ።

ዛሬ ከሁሉም ተጠሪ ተቋማት ጋር በአስተዳደር ዘርፍ ያሉ ሠራተኞች ጋር ትውውቅ ያደረጉት የሥራና ክህሎት ሚኒስትር ክብርት ሙፈሪያት ካሚል የእንኳን ደህና መጣችሁና የሚኒስቴር መሥሪያ ቤቱ እንደ ሀገር የተሰጠውን ተልዕኮና የሚያስፈጽመውን ዓላማ አስተዋውቀዋል።
በዚህ አዲስ አደረጃጀት ውስጥ አስር ያህል ተቋማት በአዲስ የተደራጅተዋል።
ተቋማችን በሆስፒታሊቲው ኢንደስትሪ ሥልጠና በመሥጠት የራሱን ከፍተኛ አስተዋጽኦ ይኖረዋል።በተለይ ደግሞ በዘርፉ ሙያዊ ክህሎት አዳብሮ መያዝ የሚችል ፤ የነበረውንም የካበተ ልምድ በመጠቀም ለወጣቶች ብቃት ያለው ሥልጠና መሥጠት የሚያስችል አበርክቶ እንደሚኖረው ታምኖበታል።
በኢንስቲትዩቶች ያሉ መምህራንና አሰልጣኞች ጋር ቀጣይ የግንኙነት ጊዜ እንደሚኖር ክብርት ሚኒስትር ሙፈሪያት ካሚል ገልጸዋል።