በአራት ከተሞች ይሰጥ የነበረው የማማከር አገልግሎት መጠናቀቁን ተከትሎ ውጤቱ ተገመገመ።

ቱሪዝም ማሰልጠኛ ኢንስቲትዩት በትግራይ ክልል በመቀሌ እና አክሱም ከተሞች እንዲሁም በኦሮሚያ ክልል ደግሞ በአዳማና ቢሾፍቱ ከተሞች ለሚገኙ የቱሪስት አገልግሎት ሰጭ ሆቴሎች ፣ሪስቶራንቶችና የቱሪዝም አስጎብኚ ድርጅቶች ይሰጥ የነበረው የማማከር አገልግሎት ተጠናቀቀ።
ኢንስቲትዩት ከየክልሎቹ ባህልና ቱሪዝም ቢሮዎች ጋር በመተባባር በአራት ቡድኖች የተቋሙን አሰልጣኞች ከሆቴልና ቱሪዝም ማህበራት ተወካይ ባለሙያዎች ጋር በማቀናጀት የተሰጠውን የማማከር አገልግሎት ከአማካሪ ቡድኑ ጋር በዛሬው ዕለት ገምግሟል፡፡
የማማከር ስራው በዋናነትም፣ በቱሪስት አገልግሎት ሰጭ ተቋማት የአገልግሎት አሰጣጥን ለማሻሻል እና ወጭ ቆጣቢ፣ ቀልጣፋ አሰራር እንዲከተሉ የሚያግዝ የአቅም ግንባታ ሥራ መሆኑን የተቋሙ ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ ይታሰብ ሥዩም ገልጸዋል፡
ከዚህም በተጨማሪ በተቋሙ እና ከልዩ ልዩ ማህበራት በመጡ ባለሙያዎች መካካል የልምድ ልውውጥ ማድረግ ያስቻለ ጭምር መሆኑን ተናግረዋል፡፡
በአራቱም ከተሞች በአጠቃላይ 58 ሆቴሎችና ሪዞርቶች፣ 14 ምግብ ቤቶች እና ስድስት የቱሪስት ድርጅቶችና ማህበራት በድምሩ 78 ተቋማት አገልግሎቱ የተሰጣቸው ሲሆን፣ ሁሉም የቱሪስት አገልግሎት ሰጭ ተቋማት በተሰጣቸው አገልግሎት ደስተኞች እንደነበሩ የአማካሪ ቡድኑ አባላት ተናግረዋል፡፡
በዚህ የማማከር ሥራ አብዛኛው ተቋማት የሰለጠነ የሰው ሀይል ጉድለት እንዳለባቸው ገልጸው የማሰልጠኛ ኢንስቲትዩቱ ሙያዊ ድጋፍ ተጠናክሮ እንዲቀጥል ተጠይቋል፡፡ በቀጣይም በሌሎች ክልሎች፣ ከተማዎች አና የቱሪስት መዳረሻ ሥፍራዎች ለሚገኙ አገልግሎት ሰጭ ተቋማት መሰል ድጋፍ እንደሚደረግ አቶ ይታሰብ ተናግረዋል ።
ትክክለኛ መረጃዎችን ለማግኘት የሚከተሉትን ማስፈንጠሪያዎችን ይጠቀሙ
ፌስቡክ፡ https://www.facebook.com/tticommunication
ቴሌግራም ፡https://t.me/tticommunication
ዌብሳይት፡ https://www.tti.edu.et/