ለኢንስቲዩቱ መምህራን የማነቃቂያ ስልጠና ተሰጠ
በሀገራችን የተጀመረውን አዲስ ምዕራፍ ወደ ተቋማችን ለማምጣት በቅድሚያ መምህራን የማነቃቂያ ስልጠና መውሰድ አስፈላጊ መሆኑን የተቋሙ ዋና ዳይሬክተር ወ/ሮ አስቴር ዳዊት ተናግረዋል፡፡
ይህ ስልጠና ከሌላው ጊዜ ለየት የሚያደርገው ስልጠናውን የኢንስቲዩቱ ቦርድ ሰብሳቢ ፕሮፌሰር አፈወርቅ ካሱ ተሞክሯቸውን በተግባር እያየን ከትንሽ ገጠር ከተማ በመነሳት የኢትዮጵያ ፕሮፌሰር እና በተለያዩ ዓለም ሀገራት በሥራቸው ተሸላሚ መሆናቸው ነው በመጠቆም መምህራን ስልጠናውን በንቃት እንዲትከታተሉ አሳስበዋል፡፡
ፕሮፈሰር አፈወርቅ ካሱ አዲሱን ዓመት ትምህርት ሰጀመር በመነቃቃት በአዲስ ምዕራፍ በአዲስ መንፈስ ከሰልጣኞቻቸው ጋር እንዲገናኙ በማሰብና ከህይወት ልምዳቸው በማስተማር እናንተም ትችላችሁ በሚል መሪ ቃል ስልጠና ሰጥተዋል፡፡
በስልጠናው የተነሱ ዋና ሀሳቦች ከዳውሮ እስከ ኮሎራዶ ጉዟዋቸውን በውስጡ ያሳለፉትን ተሞክሮ በመጥቀስ ሰፊ ስልጠና ሰጥተዋል፡፡ በተጨማሪም በትምህርትና ስልጠና እንዲሁም በምርምር ስራዎችም እንዴት መለወጥ እንዳለባቸውም ለመምህራኑ ተገጿል፡፡
ኢትዮጵያ ከሌሎች ሀገራት በኢኮኖሚ ልቃ እንዲትታይ ትልቁ የእናንተ ግኝት እና ስራ መሆኑን ተረድታችሁ እውቀትን በመፈለግ ስራ ማድረግ እንደሚጠበቅባቸው በመግለጽ‘ እኔ ከትንሽ ገጠር ከተማ ወጥቼ እዚህ ከደረስኩ እናንተ ከዚህ በላይ መስራት ትችላላችሁ’ ብለዋል፡፡
‘ተቋማችሁ 53 ዓመታት በሆቴልና በቱሪዝም ዘርፍ በርካታ ባለሙያዎችን አፍርቷል፡፡ ስለዚህ እናንተ የዚህ ዘርፍ እንቁዎች ናችሁ፡፡’ ኢትዮጵያ አፍሪካዊት የብልጽግና ተምሳሌት ለማድረግ ሰው የሆነ ሁሉ ጥረት ማድረግ እንዳለበት በመግለጽ እናንተም በራሳችሁ ዘርፍ ይህን ማሳካት እንደሚቻል ተናግረዋል፡፡
መምህራን በስልጠናው እንደተደሰቱና በንግግር ብቻ ሳይሆን በተግባር ያሳዩ መሆናቸውን በማድነቅ ለቀጣይ ሥራቸው ብዙ ትምህርት እንዳገኙበት ተናግረዋል፡፡
የፕሮፌሰር ልምድ ለሌሎች በተለያየ ዘርፍ ለሚገኙ ባለሙያዎችም በጣም አስፈላጊ መሆኑንም የጠቆሙት ተሳታፊ መምህራን ይህ ስልጠና ለብዙ ኢትዮጵያዊ ስለሚያስፈልግ ቢዳረስ በማለት አስተያየታቸውን ሰጥተዋል፡፡
Recent Comments