የአንደኛ ሩብ ዓመት ዕቅድ አፈፃፀም ሪፖርት ቀረበ
የኢፌድሪ ቱሪዝም ማሰልጠኛ ኢንስቲትዩት የ2017 ዓ.ም የአንደኛ ሩብ ዓመት ዕቅድ ሪፖርት ለተቋሙ ሰራተኞች ቀረበ።
በዚህ ፕሮግራም የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የተቋሙ ዋና ዳይሬክተር አቶ ጌታቸው ነጋሽ እንደተናገሩት የሩብ ዓመት አፈፃፀሙ በባለድርሻ አካላትና በማኔጅመንት ተገምግሞ በበጀት ዓመቱ በዘርፉ ያበረከትነው አስተዋጸኦ በስልጠና፣በጥናትና ምርምር እንዲሁም በማማከር ፣በማህበረሰብ አቀፍ አገልግሎት የጎላ እንደነበር ጠቅሰው። እንደሀገር የአጫጭር ስልጠና ፍላጎት ጋር ተያይዞ ለውጭ ሀገር ሥራ ስምሪት ያለውን የገበያ ፍላጎት ምላሽ የሚሰጥ ሥራም በስፋት መስራት የሚጠበቅብን መሆኑን ገልጸዋል።
የሀገር አቀፍ የ100 ቀን ሪፎርም ሥራዎችንና የተቋሙን የሩብ ዓመት እቅድ አፈፃፀም ሪፖርት የሥራ አመራርና አስተዳደር ዘርፍ ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ ገዛኸኝ አባተ አቅርበዋል።
ተቋማዊ የሪፎርም ሥራዎች አተገባበርን በተመለከተ የጥናትና ምርምርና ዘርፍ ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ ይታሰብ ስዩሞ አቅርበዋል።
የISO 21001:2018 አፈጻጸምን በተመለከተ የተቋሙ የአጫጭርና የማታ ዴስክ ኃላፊ እና የለውጥ አስፈጻሚ ተወካይ በአቶ ሰለሞን አሰፋ ቀርቧል። በቀረቡ ሰነዶች ከቤቱ አስተያየት ተሰጥቶ ውይይት ተደርጎበታል።
https://t.me/tticommunication
Recent Comments