ለኢንስቲትዩቱ ሠራተኞች መሰረታዊ የሳይበር ደህንነት የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ተሰጠ

በስልጠናው ስለ ማህበራዊ ሚዲያ አጠቃቀም እና ስለ ሳይበር ጥቃትና ደህንነት እንዲሁም መደረግ ስለሚገባቸው ጥንቃቄዎችየኢንፎርሜሽን ኮሚኒኬሽን ባለሙያ አቶ ሳሙኤል ገረመው የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ሰጥተዋል።
አቶ ሳሙኤል ቴክኖሎጂን በመጠቀም ዓለም እንዴት እየሰራ እንደሆነ በምሳሌ በማጣቀስ ለሰራተኛው ግንዛቤ የሚሰጡ መልዕክቶችን ሰጥተዋል።
አቶ ሳሙኤል ስለሳይበር ጥቃትና ደህንነት በቂ መረጃ መያዝ ወይም ማወቅ ወቅቱ የሚጠይቀው ዋና ጉዳይ በመሆኑ ተቋሙ በዚህ መልክ መረጃ ለሠራተኞቹ እንዲሰጥ ማመቻቸቱ የሚያስመሰግን ነው ብለዋል።
ስልጠናው ሰፋ ብሎ በቀጣይነት እንዲኖረው ሰራተኛው ጠይቋል።
በስልጠው የሸጋ ትውልድ ፕሮጀክት አስተባባሪዎች ተገኝተው መረጃውን ሰጥተዋል።
https://www.facebook.com/tticommunication