የኢንስቲትዩቱ የኢንዱስትሪ ቴክኒካል አማካሪ ቦርድ አባላት ከሀዋሳ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ አቻቸው ጋር የልምድ ልውውጥ አደረጉ።

የቱሪዝም ማሰልጠኛ ኢንስቲትዩት የኢንዱስትሪ ቴክኒካል አማካሪ ቦርድ አባላት ከሀዋሳ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ አቻቸውና ማኔጅመንት ጋር በዓለም ባንክ በሚደገፈው የEASTRIP ፕሮጀክት ዕቅድ አፈጻጸም ተግዳሮቶችና መልካም ተሞክሮዎች ላይ የልምድ ልውውጥ አደረጉ።
ፕሮጀክቱን በአግባቡ ለመጠቀም ስራዎችን ከተቋም ዕቅድ ጋር ማስተሳሰር አስፈላጊ ነው ያሉት በፖሊ ቴክኒክ ኮሌጁ የፕሮጀክቱ አስተባባሪ አቶ መለሰ ዲዳሞ በዓለም ባንክ አሰራር መሰረት የሚጠይቁ ቅድመሁኔታዎችን ማሟላት ያስፈልጋል ብለዋል።
ከዚህ በተጨማሪም ተቋማቸው ከኢንዱስትሪው ጋር ከፍተኛ ትስስር በመፍጠሩ የተሻለ አፈፃፀም እንዳለ ገልፀዋል::
የማስልጠኛ ኢንስቲትዩቱ የኢንዱስትሪ ቴክኒካል አማካሪ ቦርድ አባላትና የሜኔጅመንት አባላት በፕሮጀክቱ ስራ አፈፃፀም ላይ የሚያገጥሙ ተግዳሮቶችን በመግለፅ ውይይት ተደርጓል።
የሀዋሳ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ በሀገራችን ከዓለም ባንክ ጋር በመተባበር በፕሮጀከቱ እየተሰራ ከሚገኝባቸው ሶስቱ ተቋማት አንዱ ነው።