የማጠናከር ዘመን (consolidation Year) ተቋሙ የተሰጠውን ተልዕኮ አጠናክሮ መቀጠል እንዳለበት ተገለጸ።

የኢንስቲቲዩቱ ዋና ዳይሬክተር አቶ ጌታቸው ነጋሽ ይህ የያዝነው ዓመት የማጠንከር ዘመን/ዓመት ተብሎ መሰየሙን ገለጹ። በትምህርትና ስልጠና ፣በስልጠና ጥራት ፣የአጫጭር ስልጠና የቅበላ አቅምን ማሳደግ፣ የበጀት እጥረትን ሊቀርፉ የሚችሉ በቱሪዝምና ሆስፒታሊቲ ዘርፍ ላይ ገቢ የሚያመነጩ፣ ህብረተሰብን ተጠቃሚ የሚያደርጉ ሥራዎችን በማጠናከር ፤በዘርፉ ችግር ፈቺ ጥናትና ምርምር ማካሄድ ፤ በዘርፉ የማማከር አገልግሎት በሀገር አቀፍና ዓለም አቀፍ ደረጃ ቀዳሚና ተወዳዳሪ ሆኖ መሥራት ላይ አጠናክረን የምንይዛቸው አበይት ጉዳዮቻችን መሆናቸውን ገልጸዋል።
ለተግባራዊነቱም በቴክኖሎጂ እና በ System thinking ሁሉን አቀፍ የሆኑ ወደፊት የሚያራመዱ የሃሳብ ማመንጫ ማዕከሎችን በማጠናከር ሁሉም ሰራተኛ እና ባለድርሻ አካል ተሳትፎ አስፈላጊ ነው ብለዋል።
የባለፈውን በጀት ዓመት ዓመተ ምርታማነት በሚል መሪ ቃል ምርታችን ሰልጣኞቻችን ናቸው ብለን በልዩ ትኩረት መሥራታችን ይታወቃል።
https://t.me/tticommunication