ቱሪዝም ማሰልጠኛ ኢንስቲትዩቱ ለ55ኛ ጊዜ በሆቴልና ቱሪዝም ዘርፍ በዲግሪና በደረጃ አስመረቀ።
በምርቃት ፕሮግራሙ ላይ የተገኙት የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር ሚኒስቴር ክብርት ወ/ሮ መፈሪሃት ካሚል እንደገለጹት ለዛሬው ድርብ በዓል እንኳን አደረሳችሁ በማለት በአንድ በኩል የእናንተ ምረቃ በሌላ በኩል ደግሞ የአምራችነት ቀን በጋራ እያከበርን የሚንገኝበት ነው፡፡
አምራችነት ብዙ ግብዓትን የሚፈልግ ሲሆን ከዚህ ውስጥ አንዱና ወሳኙ የለማ የሰው ሀይል ነው፡፡ ብቁ ክህሎት የታጠቀ ሀገርን ተወዳደሪ ለማድረግ የሚያስችል የሰው ሀይል ከሌለው ለተወዳዳሪነት የሚሰጠውን ነጥብ ማግኘት አይቻልም፡፡
ከውጭ መደረሻቸውን ኢትዮጵያ አድርገው ለሚመጡት የሀገር ውስጥ ቱሪዝምን መስራት ይጠበቅብናል፤ ዘርፉን ተወዳደሪ ማድረግ ሀገርን ተወዳዳሪ ለማድረግ በሚደረገው ጉዞ የእናንተ ሀላፊነት የላቀ ነው ብለዋል፡፡
እስከ ዛሬ ያገኛችሁት እውቀት ራስን ለመቻል እና ሥራ ለመቀጠር ያግዛል፤ ሆኖም ስራ ለማግኘት ብቻ የሚሰራ ሳይሆን ትህትናን ሁል ጊዜ ተግባሩ ያደረገና አገልጋይነትን የተላበሰ ሥራውን አፍቅሮ የሚሰራ ዘርፍ ነው፡፡
ምርቃት ሲባል መጀመሪያውን ማገባደድ እንጂ ያለቀ ማለት አይደለምያሉት ሚኒስትሯ፡፡ ከእናንተ ስህተት ምንም ዕድል የሌላችሁ በመሆኑ በላቀ ቁርጠኝነትና ትጋት መለየት እንደሌለበት ለተመራቅዎች አሳስበዋል፡፡
የቱሪዝም ኢንድስትሪው እንደሀገር የቅድሚያ ቅድሚያ የተሰጠው ተግባር በመሆኑ ሞያተኞች ሆቴሎች ባለድርሻ አካላት ሁሉ በመረባረብ መስራት እንደሚያስፈልግ ክብርት ወ/ሮ መፈሪሃት ካሚል ገልጸዋል፡፡
የተቋሙ ዋና ዳይሬክተር ክቡር አቶ ጌታቸው ነጋሽ በበኩላቸው እንደገለጹት የቱሪዝም ዘርፉ በዓለም ላይ እጅግ ከፍተኛ ትኩረት ከተሰጣቸውና በየጊዜው በላቀ ደረጃ እድገት በማስገንዘብ ላይ ከሚገኙ የልማት ዘርፎች አንዱ ሲሆን ሴክተሩ ለታዳጊም ሆነ ለበለፀጉ ሀገራት፣ የውጪ ምንዛሪን በማስገኘት ገቢን የሚያሳደግ፣ ለዜጎች ሰፊ የሥራ እድል በመፍጠር ረገድ ጉልህ የሆነ አበርክቶ ያለው ዘርፍ ከመሆኑም ባሻገር በሕዝቦች መካከል፣ አዎንታዊ የባህል ልውውጥና ትስስር እንዲፈጠር፣ እንዲሁም ጠንካራ ማህበራዊ ግንኙነት እንዲጎለብት ከፍተኛ አስተዋፅኦ በማበርከት ላይ የሚገኝ የኢንዱስትሪ ዘርፍ ነው ብለዋል፡፡
የማሰልጠኛ ተቋሙ፣ በዕውቀት፣ በክህሎትና በአመለካከት የበቁ፣ በራሳቸው የሚተማመኑና ሥራ ፈጣሪ የሆኑ ዜጎችን ለማፍራት የሚያስችል አደረጃጀትና አቅም ፈጥሮ በመንቀሳቀስ ላይ የሚገኝ ሲሆን ከቴክኒክና ሙያ ስልጠና ኢንስቲትዩት ጋር በመተባበር እና የኮቪድ 19 ወረርሸኝ ያስከተለውን፣ የአካዳሚክ ካላንደር መዛባት ጫና በመቋቋም በሆቴል አስተዳደር እና በቱሪዝም ማኔጅመንት የሙያ መስኮች በመጀመሪያ ዲግሪ እንዲሁም በደረጃ 4 እና 5፣ በእንግዳ አቀባበል፣ በቤት አያያዝ፣ በምግብና መጠጥ ቁጥጥር፣ በምግብና መጠጥ መስተንግዶ፣ በዳቦና ኬክ ዝግጅት፣ በቱሪስት አስጎብኝነት እና በኩሉነሪ ኣርት ተማሪዎችን ተቀብሎ ላለፉት አራት ዓመታት ዓመታት ሲያሰለጥቸው ከቆዩት መካከል በመጀመሪያ ዲግሪ ወንድ 85 ሴት 55 ድምር 140፣ በደረጃ 4 እና 5 ወንድ 81 ሴት 100 ድምር 181 በአጠቃላይ በቀንና በማታው ፕሮግራም ወንድ 166 ሴት 155 በጥቅሉ 321 ተማሪዎችን/ሰልጣኖችን አሰልጥኖ በማብቃት በዛሬው ዕለት በመጀመሪያ ዲግሪና በደረጃ አስመርቋል፡፡ የመዉጫ ፈተና ከወሰዱ የስልጠና አጠናቃቂዎች ውስጥ 80 በመቶ የሚሆኑት ፈተናውን ያለፉ መሆናቸው ተረጋግጧል፡፡
ተመራቂዎች ሥራ ፈላጊዎች ብቻ ሳትሆኑ ሥራ ፈጣሪዎች ሆናችሁ ወደፊት የሚጠብቃችሁን የህይወት ዉጣ ውረድ በማሸነፍ የተሻለ የኑሮ ደረጃ ላይ ለመድረስ የሰነቃቸሁን ተስፋ ይዛችሁ በሙያ ክቡርነት በማመን በመረጣችሁት ሙያ ተግታችሁ እንድትሰሩ በማለት አሳስበዋል፡፡
Recent Comments