የኢንስቱትዩቱ ሰራተኞች በዓለም ቅርስነት በተመዘገበው ጢያ ትክል ድንጋይ የችግኝ ተከላ አካሄዱ፡፡
የኢንስቲትዩቱ ዋና ዳይሬክተር አቶ ጌታቸው ነጋሽ የደን ልማት የኢኮ ቱሪዝም አንዱ አካል በመሆኑ ለቱሪዝም መዳረሻ ልማት በመዳረሻዎች አካባቢ ችግኝ መትከል ለኢንቲትዩቱ ባህል ሊሆን ይገባል ብለዋል፡፡
በሀገር አቀፍ ደረጃ እስካሁን ተከናወነው የአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር የአፈር ለምነትን በማስጠበቅ ለምግብ ዋስትና እና ለአካባቢዊያዊ የአየር ለውጥ አስተዋጽኦ እያበረከተ መሆኑንም አቶ ጌታቸው ነጋሽ ገልጸዋል፡፡
የምንተክላቸው ችግኞች ለፍሬ እንዲበቁ ካለፉት ተሞክሮዎቻችን ትምህርት በመውሰድ በችግኝ አዘገጃጀትና በባለቤትነት ክትትል እንደሚደረግ የኢንስቲትዩቱ ዋና ዳይሬክተር ተናግረዋል ።
የቱሪዝም ማሰልጠኛ ኢንስቲትዩት በሀገራዊ አረንጓዴ አሻራ ላይ ንቁ ተሳታፊ ነው ያሉት የኢንስቲትዩቱ ም/ዋና ዳይሬክተር አቶ ገዛኸኝ አባተ በተከታታይ ዓመታት በቱሪስት መዳረሻዎች ላይ የችግኝ ተከላ እያካሄዱ መሆኑን ገልፀዋል ። የችግኝ ተከላ የሚከናወንባቸው የቱሪስት መዳረሻ አካባቢዎች ለሚገኙ የማህበረሰብ ክፍሎች ስልጠናና የተለያዩ የማህበረሰብ አቀፍ አገልግሎቶችን ለመስጠት እንደሚሰራ ምክትል ዋና ዳይረከተሩ ገልጸዋል፡፡
የጢያ ከተማ ማዘጋጃ ሥራ አስኪያጅ አቶ ፍቅሩ ባዩ በበኩላቸው የሚተከሉ ችግኞች ጸድቀው ለሚፈለገው አገልግሎት እንዲውሉ ከአካባቢው ማህበረሰብ ጋር በመሆን እንክብካቤ ይደረጋል ብለዋል፡፡

Recent Comments