ኢንስቲትዩቱ በውጭ ሀገር ሥራ ስምሪት ያለውን የገበያ ፍላጎት ለማሟላት በትኩረት እየሰራ እንደሆነ ተጠቆመ ::
የቱሪዝም ማሰልጠኛ ኢንስቲትዩት ከውጭ ሀገር ሥራ ስምሪት አኳያ ያለውን የገበያ ፍላጎት ለማሟላት በትኩረት እየሰራ መሆኑን አስታወቀ፡፡
ኢኒስቲትዩቱ ለሥራ ገበያ ፍላጎት ምላሽ ለመስጠትና የዜጎችን ተጠቃሚነት ለማስፋት የአሰልጣኞች ስልጠና እየሰጠ ይገኛል፡፡
በሥልጠናው የመክፈቻ መርሃ ግብር ላይ መልዕክት ያስተላለፉት የተቋሙ ዋና ዳይሬክተር አቶ ጌታቸው ነጋሽ እንደገለጹት፤ የሚሰጠው የአቅም ግንባታ ስልጠና በውጭ ሀገር ስራ ስምሪት ተጠቃሚ የሚሆኑ ዜጎች ተወዳዳሪና የተሻለ ተጠቃሚ እንዲሆኑ ማድረግ የሚያስችል ነው።
የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር የውጭ ሀገር ሥራ ስምሪቱ የዜጎችን መብት ደህንነትና ተጠቃሚነት ባረጋገጠ መልኩ እንዲሆን አቅጣጫ አስቀምጦ ተግባራዊ እየተደረገ ሲሆን በዚህ መሰረትም ኢኒስቲትዩቱ እስካሁን ለበርካታ ዜጎች ተግባር ተኮር ሥልጠናዎችን መስጠት ችሏል፡፡
ከዚህ በተጨማሪ በዘርፉ ላለው የሥራ ገበያ ፍላጎት ምላሽ ለመስጠትና የዜጎችን ተጠቃሚነት ለማስፋት የአሰልጣኞች ስልጠና እየሰጠ እንደሚገኝም ተመላክቷል፡፡
በስልጠናው ከተለያዩ ክልሎች የተወጣጡ የፖሊቴክኒክ ኮሌጅ አሰልጣኞች እንደተካፈሉም ገልፀዋል፡፡
በዚህ በጀት አመት 150 ሰልጣኞች በሦስት ዙሮች የሰለጠኑ ሲሆን የተሰጠው ሥልጠና በምግብና መጠጥ መስተንግዶ፣ በቤት አያያዝ እና በምግብ ዝግጅት ላይ ያተኮረ ተግባር ተኮር መሆኑንና ኢንስቲትዩቱ የሚሰጠውን ስልጠና በቀጣይም አጠናክሮ እንደሚቀጥል የተቋሙ አመራሮች ጠቁመዋል፡፡
የኢንስቲትዩቱ የሥልጠና እና የተቋማት አቅም ግንባታ ዴስክ ሀላፊ አቶ ተመስገን በቀለ በሦስተኛው ዙር የአሰልጣኞች ስልጠና ላይ ባስተላለፉት መልዕክት፤ ስልጠናውን ያገኙ አሰልጣኞች ወደ ተቋማቸው ሲመለሱ እንደሀገር የተሰጣቸውን ኃለፊነት እንዲወጡ አሳስበዋል፡፡
ለወቅታዊ ትኩስ የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር መረጃ ፡
ታህሳስ 5፤ 2017
በድረገጽ፡- http://mols.gov.et/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/MolsFDRE
ቴሌግራም፦ https://t.me/fdre_mols
ዋትስአፕ፡- https://whatsapp.com/channel/0029VakCgcYIyPtTbPZtDW1y
ቲክቶክ:- tiktok.com/@mols_official
ሊንክዲን፡- https://www.linkedin.com/…/ministry-of-labor-skill-fdre/
Recent Comments