የኢንስቲትዩቱ ሰልጣኞች የብሔር ብሔረሰቦችን በዓል አከበሩ።
ቱ.ማ.ኢ
የፌዴራል ቱሪዝም ማሰልጠኛ ኢንስቲትዩት ሰልጣኞች 19ኛውን የብሔር ብሔረሰቦች በዓል በልዩ ልዩ ዝግጅቶች አከበሩ። የኢንስቲትዩቱ የሥራ አመራር እና አስተዳደር ዘርፍ ም/ዋና ዳይሬክተር አቶ ገዛኸኝ አባተ ለሰልጣኞች ባስተላለፉት መልዕክት ቱሪዝም ማሰልጠኛ ኢንስቲትዩት” ትንሿ ኢትዮጵያ” ናት ከየትኛውም የሀገሪቱ ክልሎች የመጡ ሰልጣኞች የሚስተናገዱበት፣ በስልጠና እና በሥራው ዓለም ሲሰማሩ የኢትዮጵያን ታሪክ፣ባህል፣ቅርስ የሚያስተዋውቁ እንዲሁም ከተለያየ የዓለም ክፍልም ሆነ የሀገራችን ጎብኚ እንግዳ የሚቀበሉና የሚያስተናግዱ ባለሙያዎችን የሚያፈራ በመሆኑ ኢትዮጵያን ለማወቅና ለማስተዋወቅ መልካም አጋጣሚ ይፈጥርላቸዋልብለዋል።
ም/ዋና ዳይሬክተሩ አክለውም ቱሪዝም ለሰላም ሰላም ለቱሪዝም የጀርባ አጥንት ነው። በሀገራችን ቱሪዝም ከአምስቱ የኢኮኖሚ ዘርፎች አንዱ ሆኖ በልዩ ትኩረት እየተሰራ ያለው ሥራ የሚደነቅ ነው፤ በዘርፉ ተጠቃሚ ለመሆን ሁላችንም ለሰላም ዘብ መቆም አለብን ብለዋል።
ሰልጣኞች በተለያየ የብሔር ብሄረሰቦች ባህላዊ አልባሳት ደምቀው በዓሉን ያደመቁት ሲሆን በዓሉ በሻማ ማብራት እና በኢትዮጵያ ባንዲራ ያሸበረቀ ኬክ እና ዳቦ በመቁረስ ስነስርዓት ተፈጽሟል።
ትክክለኛ መረጃዎችን ለማግኘት የሚከተሉትን ማስፈንጠሪያዎችን ይጠቀሙ
ፌስቡክ፡ https://www.facebook.com/tticommunication
ቴሌግራም ፡https://t.me/tticommunication
ዌብሳይት፡ https://www.tti.edu.e
Recent Comments