በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ለሚገኙ ለተመረጡ ሆቴሎች የማማከር አገልግሎት እየተሰጠ ነው።
ቱማኢ

ቱሪዝም ማሰልጠኛ ኢንስቲትዩት ከአዲስ አበባ ባህል ቱሪዝም ኪነ ጥበብ ቢሮ ጋር በመተባበር በከተማው የሚገኙ እና የተመረጡ 84 ሆቴሎችን አቅም የሚገነባ የማማከር አገልግሎት እየተሰጠ ነው።
አገልግሎቱ በዋናነት በእንግዳ አቀባበል እና መስተንግዶ ፣ በምግብ አዘገጃጀት ፣ በቤት አያያዝና ንፅህና አጠባበቅ ዙሪያ የማማከር ሥራ እየተሰራ መሆኑን የቱሪዝም ማሰልጠኛ ኢንስቲትዩት ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ ይታሰብ ስዩም ገልጸዋል።
እንደ ም/ዋና ዳይሬክተሩ ገለጻ አገልግሎቱ ከአዲስ አበባ ከተማ በተወጣጡ 20 የሆቴልና ቱሪዝም ባለሙያዎች የኢትዮጵያ ሆቴል ምደባ መስፈርትን መሰረት በማድረግ ስልጠና በመስጠት ወደ የተቋማቱ ሄደው የማማከር አገልግሎት እንዲሰጡ ተደርጓል።
አገልግሎቱ መጭዉን የአፍሪካ ህብረት ስብሰባ ምክንያት በማድረግ ጭምር የተሰጠ ሲሆን፤ ሆቴሎች የኮከብ ደረጃ እንዲያገኙ እና ያላቸውንም እንዲያሻሽሉ የሚያግዝ ነው።
የማማከር አገልግሎት ካገኙ ተቋማት መካከል የታሪካዊዉ ጣይቱ ሆቴል እና የጃቫኒ ሆቴል ሥራ አስኪያጆች እንደገለፁት ተቋሙ ተነሳሽነት በመውሰድ እንደዚህ አይነት የማማከር አገልግሎት መሰጠቱ የሚበረታታ መሆኑን በመግለፅ ከዚህ በኋላ በአጫጭር ስልጠና እና በማማከር አገልግሎት ዙሪያ ከተቋሙ ጋር አብረው እንደሚሰሩ ተናግረዋል።
ትክክለኛ መረጃ ለማግኘት የሚከተሉትን ሊንክ በመጠቀም የፌስቡክ ገጻችን ይጎብኙ፣ ላይክ፣ ሼር ያድርጉ
We kindly invite you to join our telegram group https://t.me/tticommunication and like, follow, and share the Facebook page https://www.facebook.com/tticommunication