የማሰልጠኛ ኢንስቲትዩቱ ሠራተኞች በሀገራዊ ጉዳዮች ላይ ውይይት አካሄዱ ቱ.ማ.ኢ መጋቢት 23/2017 ዓ.ም የቱሪዝም ማሰልጠኛ ኢንስቲትዩት ሠራተኞች “ትላንት፣ ዛሬና ነገን ለኢትዮጵያ ልዕልና” የነገ ተስፋዎች በሚል መሪ ቃል በወቅታዊ ጉዳዮች ላይ ውይይት አድርገዋል።

በመድረኩ የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የኢንስቲትዩቱ ዋና ዳይሬክተር አቶ ጌታቸው ነጋሽ መጋቢት ወር በሀገራችን አንኳር ፖለቲካዊ ሁነቶች የተከናወኑበት፤ መጋቢት 24 ታላቁ የኢትዮጵያ የህዳሴ ግድብ መሰረት ድንጋይ የተጣለበት ፤ የፖለቲካ ለውጡ መሪ ጠቅላይ ሚንስትር አብይ አህመድ ሀገራችንን ለመምራት በፓርላማ ፊት ቃል የገቡበት ሁለት ታላላቅ ሁነቶች የተስተናገዱበት ነው ብለዋል፡፡
የመወያያ ሰነዱን የኢንስቲትዩቱ የስልጠናና አቅም ግንባታ ዘርፍ ም/ዋ/ዳይሬክተር አቶ ሀብታሙ ክብረት በኢኮኖሚ ፣ ማህበራዊ ፣ በፖለቲካዊ እና ዲፕሎማሲ ያሉ ወቅታዊ ጉዳዮች ላይ ገለፃ አድርገዋል።
በገለጻቸውም በተለይ በኢኮኖሚ ዘርፍ ከፍተኛ ትኩረት ከተሰጣቸው ዘርፎች መካከል የቱሪዝም ዘርፉ ኢትዮጵያን ምርጥ የዓለም ቱሪስት መዳረሻ ለማድረግ የተሰሩ አዳዲስ መዳረሻዎች፣ የቱሪስት አገልግሎት ሰጪ ተቋማት፣ እድሳት የተደረገላቸው የአጼ ፋሲል ግንብ እና ብሔራዊ ቤተመንግስትን ለአብነት አንስተዋል፡፡
ሠራተኞችም በቀረበው ሰነድ መነሻነት አስተያየት የሰጡ ሲሆን አቶ ጀማል ሙሐመድ በሰባት ዓመት ውስጥ የተሰሩት ሥራዎች ሀገራችን ማደግ የምትችል፣ እንደሆነች ያሳየን ነው ብለዋል።
አቶ ታደሰ ሞላ በበኩላቸው እንደሀገር በተሰሩ ሥራዎች ላይ ውይይት ማድረጋችን ሁሉም ሰው እውቀት እንዲኖረው የሚያስችል ሲሆን እንደሀገር የተሰሩ ሥራዎች በውጭ ሀገር አይተን የምንመኘው አይነት ለውጥና እድገት ነበር ብለዋል።
በመጨረሻም ቱሪዝም አንዱ የኢኮኖሚ ዘርፍ ሆኖ ከአምስቱ ቁልፍ የኢኮኖሚ ምሶሶዎች መካተቱ ለዘርፉ የተሰጠውን ትኩረት የሚያሳይ ነው፤ ቱሪዝም ከሰላም ጋር የተዛመደ በመሆኑ ለሀገራችን ሁለንተናዊ ሰላም ሁሉም የበኩልን ድርሻ ይወጣ የሚል መልዕክት ተላልፏል፡፡
ትክክለኛ መረጃዎችን ለማግኘት የሚከተሉትን ማስፈንጠሪያዎችን ይጠቀሙ
ፌስቡክ፡ https://www.facebook.com/tticommunication
ቴሌግራም ፡https://t.me/tticommunication
ዌብሳይት፡ https://www.tti.edu.et