ሆ/ቱ/ሥ/ማ/ማ መጋቢት 30/2013 ዓ.ም
ሀረር ጥንታዊት፣ ከተቆረቆረች 1,000 ዓመት በላይ የሆናት ከቀደምት የአገራችን ከተሞች አንዷናት፡፡
የሁለተኛ ዓመት የቱሪዝም ሰልጣኞች በዚህች ከተማ የሚገኙ የባህልና ቅርስ ሀብቶችን እንዲሁም በቱሪስት የሚጎበኙ ስፍራዎችን የከተማው የቱር ጋይድ ባለሙያ አቶ አዮብ አምዴ ሲሆኑ ከከተማው አመሠራረት ጀምሮ ስለጀጎል ግንብና ስለአምስቱ የጀጎል በሮች ማብራሪያ ተሰጥተዋል፡፡
ሁለት የመንግስት እና አንድ የግል ሙዚዬም ውስጥ ያሉ ቅርሶችና ስለጥንታዊ የሀረር ቤቶች አሰራር ሰፊ ማብራሪያ አስጎብኚው ሰጥተዋል።
በተጨማሪም ከተማዋ የምትታወቅበትን የጅብ መመገብና ጅብን እንዴት ማላመድ እንደቻሉ ለሰልጣኞቻችን ገለፃ ተደርጎላቸዋል።