ሆ/ቱ/ሥ/ማ/ማ ሚያዝያ 20/2013 ዓ.ም የሆቴልና ቱሪዝም ሥራ ማሰልጠኛ ማዕከል የሁለተኛ ዓመት ቱሪዝም ማኔጅመንትና ቱሪዝም ማርኬትንግ ሰልጣኞች ትምህርታዊ ጉብኚት በአንድነት ፓርክ አደረጉ፡፡
የአንድነት ፓርክ በታላቁ ቤተ መንግስት ግቢ ውስጥ የሚገኝ ሲሆን በውስጡም ልዩ ልዩ የታሪክ፣ የተፈጥሮ እና የባህል መስህቦችን አጠቃሎ የያዘ ነው፡፡ የፓርኩ አስጎበኚ የሆኑት አቶ ካሊድ አህመድ እንደገለጹት ፓርኩ ከያዛቸው መስህቦች መካከል ቤተ መንግስቱ ከተቆረቆረበት ጊዜ ጀምሮ የተሰሩ ታሪካዊ ህንጻዎች፣ የዱር እንስሳት ሥፍራዎች፣ የክልሎችን ባህላዊና ተፈጥሮዊ መስህቦች በጥቂቱ የሚያስተዋውቁ እልፍኞች፣ የአገር በቀል ዕጸዋት ሥፍራ፣ የአረንጓዴ ቦታ እና ልዩ ልዩ አገልግሎት መሰጪያ አደባባይ ዋና ዋናዎቹ ናቸው፡፡
በተጨማሪም ሰልጣኞች የወዳጅነት ፓርክንም ጎብኝተዋል