ሆ.ቱ.ሥ.ማ.ኢ መስከረም 07/2012 አስ አሌ ሀይቅ የጨው ሜዳ በመባል ይታወቃል። 1200 ስኩዌር ኪሎሜትር በጨው የተሸፈነ ነው። ይህ ቦታ ከባህር ወለል በታች 116 ሜትር ጥልቀት ሲኖረው ይህም በዓለም ሁለተኛ ደረጃ ላይ እንዲገኝ አስችሎታል። ኢትዮጵያን የተቃርኖ ምድር እንድትሰኝ ካስቻሏት ምክንያቶች መካከል አንዱ የዚህ ቦታ መገኛ መሆኗ ነው። ማለትም በከፍታ ደረጃ ራስ ዳሸን 4543 ሜትር ከባህር ወለል በላይ ሲሆን በዝቅታ ደረጃ ደግሞ ዳሎል ከባህር ወለል በታች 116 ሜትር ጥልቀት ያለው መሆኑ ሀገራችንን በእንግሊዝኛ “Land of contrast ” እንድትባል አድርጓታል ።
የአስ አሌ ሀይቅን ልዩ የሚያደርገው ሌላ ምክንያት የጨው ማውጣት ሂደትና የወጣውን የአሞሌ ጨው ምርት በግመል የማጓጓዝ ልዩ ትዕይንት (ወደ 200 የሚሆኑ ግመሎችን በአንድ ጊዜ የሚያጓጉዙበት ሂደት (ሲራራ ንግድ/Caravan))ዋናው የቱሪስት መስህብ ነው።
የአካባቢው ማህበረሰብም በቱሪዝም እንቅስቃሴው በከፍተኛ ሁኔታ እየተሳተፉ ይገኛሉ።
በጨው ሜዳው ላይ ጠዋትና ማታ ፀሀይ ስትወጣና ስትጠልቅ በአካባቢው ላይ የሚታየው ድባብ እጅግ አስገራሚ ነው።