የቱሪዝምና የሆቴል ኢንዱስትሪ ዘርፉን የሚመጥን ብቁ ባለሙያ ለማፍራት የተጀመሩ ስራዎች ተጠናክረው እንደሚቀጥሉ የስራና ክህሎት ሚኒስቴር አስታወቀ።
የቱሪዝምና የሆቴል ኢንዱስትሪ ዘርፉን የሚመጥን ብቁ ባለሙያ ለማፍራት የተጀመሩ ስራዎች ተጠናክረው ይቀጥላሉ
ቱሪዝም ማሰልጠኛ ኢንስቲትዩት 11ኛውን የቱሪዝምና እንግዳ ተቀባይነት ሳምንት “ቱሪዝም ለሀገራዊ መግባባት” በሚል መሪ ሃሳብ በተለያዩ መርኃ ግብሮች ማክበር ጀምሯል።
መርኃ ግብሩ ለሶስት ተከታታይ ቀናት የሚቆይ ሲሆን በዛሬው ፕሮግራም በአፋር፣ በሀረሪ፣ በሲዳማ እና ጋምቤላ ክልሎች የሚኖሩ ማህበረሰቦች ባህላዊ ምግቦቻቸውንና መገልገያ ዕቃዎቻቸውን ለዕይታ አቅርበዋል።
በዚሁ ወቅት የስራና ክህሎት ሚኒስትር ዴኤታ ዶክተር ተሻለ በሬቻ በተለያዩ የስራ ዘርፎች ብቃት ያላቸውን ሙያተኞች ለማፍራት ሚኒስቴሩ ክህሎትን መነሻ ያደረገ ስራ እየሰራ መሆኑን አስታውቀዋል።
በቱሪዝምና እንግዳ ተቀባይነት ሳምንቱ በዘርፉ ብቁ ሙያተኞችን ለማፍራት ብሎም የሀገሪቱን ባህል ለማስተዋወቅ ያግዛል ነው ያሉት።
የቱሪዝም ዘርፍ አገልግሎት ላይ የተመሰረተ ቢሆንም እንደ ሀገር በዘርፉ ያለው አገልግሎት አሰጣጥ ከሌሎች ሀገራት ጋር ሲወዳደር ብዙ ስራዎች መስራት እንደሚጠበቅብን አመላካች ነው ብለዋል።
በሀገሪቱ የቱሪዝም መዳረሻዎችና ሆቴሎች እየተስፋፉ በመሆናቸው ዘርፉ ለሀገር ተገቢውን ጠቀሜታ እንዲያስገኝ ሙያተኞች በዕውቀትና በክህሎት ብቁ እንዲሆኑ መስራት ተገቢ መሆኑን ጠቅሰዋል።
ለዚህም ሚኒስቴሩ በሀገሪቱ እየተስፋፋ ያለውን የቱሪዝምና የሆቴል ኢንዱስትሪ የሚመጥን ብቁ ባለሙያ ለማፍራት የተጀመሩ ስራዎችን አጠናክሮ እንደሚቀጥል ገልጸዋል።
የኢንስቲትዩቱ ዋና ዳይሬክተር አቶ ጌታቸው ነጋሽ በበኩላቸው ተቋሙ በቱሪዝም ዘርፍ ብቁ ሙያተኞችን ለማፍራትና የሀገሪቱን ባህላዊ ምግቦች በሚፈለገው ደረጃ ለማስተዋወቅ የጀመራቸውን ስራዎች አጠናክሮ መቀጠሉን ተናግረዋል፡፡
ለዚህ ይረዳው ዘንድ በዘርፉ ስልጠና ከመስጠት ባለፈ በጥናትና ምርምር የተደገፉ ውጤቶችን ለማውጣት የጀመራቸውን ስራዎች አጠናክሮ እንደሚቀጥል አስታውቀዋል።
ኢንስቲትዩቱ በዘርፉ ተጨባጭ ለውጥ ለማምጣት በየዓመቱ የቱሪዝምና እንግዳ ተቀባይነት ሳምንት እንደሚያካሂድ ገልጸው የዛሬው ተመሳሳይ ፕሮግራም የዚሁ አካል መሆኑን ጠቁመዋል።
ለሶስት ቀናት በሚቆየው መርኃ ግብር በሆቴልና ቱሪዝም ዘርፍ በሚገኙ ባለሙያዎች መካከል ልዩ ልዩ የክህሎት ውድድር፣ ኤግዚቢሽንና ሲምፖዚየም መዘጋጀቱን ተናግረዋል፡፡
በዚህም የሰልጣኞችንና የአሰልጣኞችን የሙያ ብቃት ለማሻሻል ጥረት እንደሚደረግ ዋና ዳይሬክተሩ አብራርተዋል።
መረጃዎቻችንን፦
በዩቲዩብ፡- https://www.youtube.com/channel/UCSjaw-eGJSkvcXHyTpQyT1Q
በቴሌግራም፡- https://t.me/EthiopianNewsA
በድረገጽ፡- https://www.ena.et/
በትዊተር፡- https://twitter.com/ethiopiannewsa?lang=en
የኢዜአ ዜናዎችን በአጭር የስልክ መልዕክት ለማግኘት፡- 9111
ፈረንሳይኛ ድረ-ገጽ https://www.ena.et/web/fre
አረብኛ ድረ-ገጽ https://www.ena.et/web/ara
በአፋን ኦሮሞ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/TajaajilaOduuItoophiyaa/
በትግሪኛ ፌስቡክ፦ https://ww.facebook.com/ethiopianewsagencytigrigna/
በአፍ ሱማሌ ፌስቡክ፦ https://www.facebook.com/ethiopianewsagencyafsoomaali
በአፍ ሱማሌ ድረ-ገጽ፦ https://www.ena.et/web/som
በአፋርኛ ፌስቡክ፦ https://www.facebook.com/ethiopianewsagencyqafarafa
በአፋርኛ ድረ-ገጽ፦ https://www.ena.et/web/aar አድራሻዎቻችን ያገኟቸዋል።

Recent Comments