ሆ.ቱ.ማ.ኢ ታህሳስ 03/2012
በኢንስቲትዩቱ ቱሪዝም ትምህርት ክፍል የሚሰለጥኑ አዲስ ሰልጣኞች በአዲስ አበባ ከተማ የሚገኙ የቱሪስት መስህቦችን እና ብሔራዊ ሙዚየምን ጎበኙ፡፡
ጉብኝቱን የሚመሩት የቱሪዝም ትምህርት ክፍል መምህራን ለሰልጣኞቹ በከተማዋ የሚገኙ ባህላዊ፣ሃይማኖታዊና ታሪካዊ ቅርሶችን አስጎብኝተዋል፡፡
አንዳንድ ሰልጣኞች ከጉብኙቱ በኋላ እንደገለጹት ጉብኝቱ ለቀጣይ ትምህርታቸው በጣም እንደሚጠቅምና ስለሃገራቸው ቀደም ያለ ታሪክ ለማወቅ እድል እንደፈጠረላቸው ተናግረዋል፡፡
በቀጣይ ቀናት ከአዲስ አበባ ውጪ ያሉ የቱሪስት መዳረሻ ስፍራዎችንም ይጎበኛሉ ተብሎ ይጠበቃል፡፡
Recent Comments