ኢንስቲትዩቱ በቂርቆስ ክ/ከተማ ወረዳ 11 ለሚገኙ እስልምና እምነት ተከታዮች የኢፍጣር ፕሮግራም አካሄደ ። ቱሪዝም ማሰልጠኛ ኢንስቲትዩት ከገነት ሆቴል ጋር በመሆን በቂርቆስ ክ/ከተማ ወረዳ 10 ለሚገኙ የእስልምና ሀይማኖት ተከታዮች የኢፍጣር መርሐግብር አካሄደ ።በመርሐ ግብሩ ላይ የተገኙት የኢንስቲትዩቱ የጥናት ምርምርና ማማር ዘርፍ ም/ዋና ዳይሬክተር አቶ ይታሰብ ስዩም ለጾሙ የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላልፈው ማሰልጠኛ ተቋሙ በሥራ ዕድል ፈጠራ፣ በስልጠናና ማዕድ በማጋራት የአካባቢውን ማህበረሰብ ተጠቃሚ የሚያደርጉ ተግባራትን በትኩረት እያከናወነ ይገኛል ብለዋል።
የቂርቆስ ክ/ከተማ ወረዳ 11 ሥራ አስኪያጅ አቶ ደህንነት ገብሩ በበኩላቸው ማሰልጠኛ ኢንስቲትዩቱ በሁሉም በዓላት ማዕድ በማጋራት ፣ የአካባቢውን ማህበረሰብ ተጠቃሚ የሚያደርግ አጫጭር ጊዜ ስልጠና በመስጠት እና የፈጣን ምግቦች መስሪያ ማሽን በመስጠት ጭምር እያገዘ እንደሚገኝ ምስጋና ይገባዋል ብለዋል።
የመርሐ ግብሩ ተሳታፊዎችም ኢንስቲትዩቱ ከማህበረሰቡ ጋር ተቀራርቦ እየሰራ ላለው ሥራ ምስጋና አቅርበዋል ።
ትክክለኛ መረጃዎችን ለማግኘት የሚከተሉትን ማስፈንጠሪያዎችን ይጠቀሙ
ፌስቡክ፡ https://www.facebook.com/tticommunication
ቴሌግራም ፡https://t.me/tticommunication
ዌብሳይት፡ https://www.tti.edu.et


Recent Comments