ጥር 4/2015 ዓ.ም ሀዋሳ የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር ከሲዳማ ክልል ጋር በመተባበር ኢንቲትዩቶች፣ ኮሌጆች፣ የአነስተኛና ጥቃቅን ኢንተርፕራይዞች የተሳተፉበት ኤግዚቢሽንና ባዛር ላይ ቱሪዝም ማሰልጠኛ ኢንስቲትዩት ተሳትፎ እያደረገ ይገኛል።

ኤግዚብሽኑን የከፈቱት ክቡር አቶ ንጉሱ ጥላሁን የዚህ ኤግዚቢሽን ዓላማ የገበያ ትስስር መፍጠር፣ የቴክኖሎጂ ሽግግር እና የሥልጠና ተቋማት ክፍተትን በመለየት የጋር የትብብር ሥራ እንዲሰሩ እድል ለመስጠት ነው ብለዋል።
ቱሪዝም ማሰልጠኛ ኢንስቲትዩትም በኤግዚብሽኑ ራሱን ያስተዋወቀ ሲሆን በቱሪዝምና በሆቴል ሥልጠና አብረውን ሊሰሩ የሚችሉ ድርጅቶችና ኮሌጆች ጋር ለመገናኘት እድል አግኝቷል።
ኤግዚቢሽኑ በአገር አቀፍ ደረጃ ለመጀመሪያ ጊዜ የተዘጋጀ ሲሆን እስከ ጥር 9/2015 ዓ.ም ለጎብኚዎች ክፍት ሆኖ ይቆያል።