የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር የ2017 በጀት ዓመት የመጀመሪያ ግማሽ ዓመት የዘርፎች አፈፃፀም ግምገማን አጠናቆ የተጠሪ ተቋማትን አፈፃፀም መገምገም ጀምሯል፡፡ በዚህም የቱሪዝም ማሰልጠኛ ኢንስቲትዩት 2017 በጀት ዓመት የመጀመሪያ ግማሽ ዓመት የሥራ አፈፃፀም ቀርቦ ውይይት ተደርጎበታል፡፡የሥራና ክህሎት ሚኒስትር ክብርት ወ/ሮ ሙፈሪሃት ካሚል እንደገለጹት ኢንስቲትዩቱ የጀመራቸው የሪፎርም ተግባራት ተስፋ ሰጪ ናቸው፡፡

በቀጣይ በቱሪዝም ዘርፍ የሰለጠነ የሰው ሃይል አቅርቦትና ፍላጎት ያለመጣጣም በመኖሩ ነባራዊ ሁኔታውን ያገናዘበና የበይነ መረብ የሥልጠና አማራጮችንም ጭምር የሚጠቀም የሰው ኃይል ልማት ተግባራዊ ማድረግ ያስፈልጋል፡፡
በዘርፉ በልምድ የተገኘ ሙያን ቴክኒካዊና ባህሪያዊ ብቃቶችን መዝኖ እውቅና መስጠት ላይ በትኩረት መሰራት እንደሚገባ ያመላከቱት ክብርት ሚኒስትር ከእንግሊዘኛ በተጨማሪ የውጭ ቋንቋዎች ሥልጠና ላይ የተጀመሩ ሥራዎችን ማጠናከር ይገባል ብለዋል፡፡
የባህል ምግቦችን በጥናት ለይቶ ወደ ሆቴሎች ሜኑ ለማስገባት የተጀመሩ ሥራዎች ባህሉን ከመጠበቅ ባሻገር ለበርካታ ዜጎች የሥራ ዕድል ለመፍጠርና አካባቢያዊ ኢኮኖሚውን ለማነቃቃት ከፍተኛ ፋይዳ ያለው በመሆኑ ተጠናክሮ መቀጠል እንዳለበትም አመላክተዋል፡፡
ትክክለኛ መረጃዎችን ለማግኘት የሚከተሉትን ማስፈንጠሪያዎችን ይጠቀሙ
ፌስቡክ፡ https://www.facebook.com/tticommunication
ቴሌግራም ፡https://t.me/tticommunic