መጋቢት 29/2014ዓ.ም ለተቋማችን የህፃናት ማቆያ፣ ለጤና እንክብካቤ ክፍል እና ለሠራተኛው የስፖርት መዝናኛ የሚሆን 25 ዓይነት ያለው ቁሳቁስ ደጋፍ ያደረገው

KFW የተባለው የጀርመን ተራዳኦ ድርጅት ሲሆን የድርጅቱ ሃላፊዎች በየካቲት ወር መጥተው ተቋሙን ክጎበኙ በኋላ ይህ የመጀመሪያው ድጋፍ መሆኑ ነው።
ኢንስቲትዩቱ በአዲሱ አደረጃጀት ለሥራና ክህሎት ሚኒስቴር ተጠሪ ከሆነ ጀምሮ በርካታ ሥራዎች እየተከናወኑ በመሆናቸው ኃላፊዎቹ ለዘርፉ ለሰጡት ትኩረት ተቋሙ ያመሰግናል።
የቁሳቁስ ድጋፉ ከአምስት ሚሊየን ብር በላይ የሚገመት ሲሆን በቀጣይም ቃል የተገባው ድጋፍ ተቋሙን የልህቀት ማዕከል በማድረግ ለሆስፒታሊቲ ኢደስትሪው ከፍተኛ እገዛ ይኖረዋል ተብሎ ይጠበቃል።